Saturday, 19 August 2017 12:43

“ጋላክሲ ኖት 8” በመጪው ረቡዕ በገበያ ላይ ይውላል

Written by 
Rate this item
(0 votes)

 የደቡብ ኮርያው የአለማችን ግዙፍ የኤሌክትሮኒክስ ኩባንያ ሳምሰንግ፤ በብዙዎች ዘንድ በጉጉት ሲጠበቅ የቆየውን አዲሱን ምርቱን ጋላክሲ ኖት 8ን ከመጪው ረቡዕ ጀምሮ ለአለማቀፍ ገበያ እንደሚያቀርብ ይጠበቃል፡፡
የተለያዩ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎችና የዜና ምንጮች ባሰራጯቸው መረጃዎች እንዳሉት፣ ሳምሰንግ ጋላክሲ ኖት 8 በደብዛዛ ብርሃንና በከፍተኛ ርቀት፣ እጅግ ጥራት ያላቸው ፎቶግራፎችን ማንሳት የሚያስችሉ ባለ አስራ ሁለት ሜጋፒክስልና ባለ አስራ ሶስት ሜጋፒክስል ሁለት ካሜራዎች የተገጠሙለት ነው፡፡
6 ጊጋ ባይት ራም እና 64 ጊጋ ባይት ሚሞሪ የተገጠመለት እና የተለያዩ የቀለም አማራጮች ያሉት ነው የተባለው ጋላክሲ ኖት 8፣ መጠኑም በገበያ ላይ ከሚገኙት የጋላክሲ ኤስ ሞዴሎች ከፍ ያለ እንደሚሆን የተነገረ ሲሆን፣ ቅርጹም ከጋላክሲ ኤስ 8 ጋር ተመሳሳይ በሆነ መልኩ የተሰራና ከርቭ ያለው ነው ተብሏል፡፡
ስክሪኑ 6.3 ኢንች ስፋት ያለው ጋላክሲ ኖት 8፣ ረቡዕ ዕለት ኒውዮርክ ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ በይፋ ተመርቆ በገበያ ላይ እንደሚውል የሚጠበቅ ሲሆን፣ የመሸጫ ዋጋውም እስከ 1 ሺህ ዶላር ሊደርስ እንደሚችል የተለያዩ ድረገጾች ዘግበዋል፡፡

Read 1583 times