ሚዩዚክ ሜይዴይ ከኢትዮጵስ ኮሌጅ ጋር በመተባበር ነገ ከቀኑ 8፡00 ጀምሮ በብሔራዊ ቤተ- መፃሕፍትና ቤተ - መዛግብት ኤጀንሲ አዳራሽ የበሁሉም አለበል ስራ በሆነው “ታሪክን በቅኔ” በተሰኘ መፅሐፍ ላይ ውይይት ያካሂዳል፡፡ በዕለቱ ለውይይቱ የመነሻ ሀሳብ የሚያቀርቡት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በፎክሎር የ3ኛ ዲግሪ ተማሪ የሆኑት አቶ ሰለሞን ተሾመ ሲሆኑ ፍላጎት ያለው በውይይቱ ላይ እንዲሳተፍ ሚዩዚክ ሜይዴይ ጋብዟል፡፡