Saturday, 19 August 2017 12:58

“ፍትህ ያጣ እንባ” መፅሐፍ ዛሬ ይመረቃል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(1 Vote)

  ሴት ልጅህን በመቀስ ገርዘሀል በሚል የሀሰት ክስ በአሜሪካ ለ10 ዓመት ታስረው በቅርቡ የወጡት ኢትዮጵያዊ ካሊድ አደም ያዘጋጁትና እውነተኛ ታሪካቸውን የሚያሳየው “ፍትህ ያጣ እንባ” መፅሐፍ ዛሬ ጠዋት ካዛንቺስ በሚገኘው ጁፒተር ኢንተርናሽናል ሆቴል ይመረቃል መፅሐፉ ስለክሱ መነሻና መድረሻ፣ “ኢ-ፍትሃዊ” ስለሚሉት ፍርድ አሰጣጥ፣ እስር ቤት ስላሳለፉት አስር የመከራና የግፍ ዓመታት ፖለቲካዊ ይዘት ስላለው ስለዚህ የክስ ሂደት ስለደቡብ አፍሪካዊቷ ባለቤታቸውና ስለአጠቃላይ ህይወታቸው የሚተነትን ነው ተብሏል፡፡ ይህ የእውነተኛ ታሪክ መፅሐፍ ከኢትዮጵያዊያን አልፎ ዓለም እንዲማርበት ወደ እንግሊዝኛ ይመለሳልም
ተብሏል፡፡ በ455 ገፅ የተመጣጠነው መፅሐፉ በ170 ብር እና በ22.60 ዶላር ለገበያ ቀርቧል፡፡ በምርቃት ስነ-ስርዓቱ ላይ የህግ ባለሙያዎች፣ ደራሲያን፣ የኪነ-
ጥበብ ሰዎችና ሌሎችም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት ይመረቃል ተብሏል፡፡

Read 2605 times