Saturday, 26 August 2017 12:11

በቀጣዩ ዓመት ሁለት የኢታኖል ፋብሪካዎች ግንባታ ይጀመራል

Written by  መታሰቢያ ካሳዬ
Rate this item
(1 Vote)

     በመጪው አመት ሁለት የኢታኖል ፋብሪካዎች ግንባታ እንደሚጀመር ከኢትዮጵያ የማዕድን፣ ነዳጅና ባዮፊውል ኮርፖሬሽን የተገኘ መረጃ አመለከተ፡፡
1.4 ሚሊዮን ብር በሆነ ወጪ ይገነባሉ የተባሉት እነዚህ ፋብሪካዎች፤ ከስኳር ምርት በሚገኘው ሞላሰስ በተሰኘ ተረፈ ምርት ኢታኖልን በማምረት፣ ከነዳጅ ጋር ተቀይጦ ጥቅም ላይ እንዲውል ያደርጋሉ ተብሏል፡፡
የአገሪቱ የነዳጅ ፍላጎት ከ10 እስከ 15 በመቶ እያደገ ከመሆኑ አንፃር፣ ለዚህ የሚወጣው የውጪ ምንዛሬ ከዓመት ወደ ዓመት በከፍተኛ መጠን እየጨመረ ሲሆን ይህንን ችግር ለመቅረፍም ፋብሪካዎቹ በሚያመርቱት የኢታኖል ምርት የውጭ ምንዛሬ ለመቀነስ እንደታሰበ ተነግሯል፡፡
የሁለቱ ፋብሪካዎች የግንባታ ወጪ ከኢንዱስትሪ ልማት ፈንድ በሚገኝ ብድር እንደሚሸፈን ያመለከተው መረጃው፤ የሁለቱም ግንባታ የአንድ አመት ተኩል ጊዜ እንደሚወስድና በ2011 አጋማሽ ላይ ወደ ምርት እንደሚገቡ ጠቁሟል፡፡

Read 1713 times