Saturday, 02 September 2017 12:34

“ፍንጭ” ከ25 ዓመታት በኋላ በድጋሚ ታተመ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(2 votes)

የአዲስ አድማስ የ“እንጨዋወት አምድ የረዥም ዘመን ቋሚ አምደኛ በሆነው ደራሲ፣ ወግ ፀሐፊና፣ ተርጓሚ ኤፍሬም እንዳለ፤ ከ25 ዓመታት በፊት “ፍንጭ” በሚል ተተርጉሞ ለንባብ የበቃው የሮበርት ሉድለም “THE HOLCROFF CONVENANT” የተሰኘ ረጅም ልቦለድ መፅሐፍ በድጋሚ ታትሞ ለገበያ ቀረበ፡፡
“በልብ አንጠልጣይ የአፃፃፍ ስልቱ በዘመናዊ ስነ - ፅሁፍ ቀዳሚ ነው የሚባለው ሮበርት ሉድለም፤ ድንቅ ከሚባሉለት መፅሐፍት አንዱ “ዘ ሆልክሮፍት” ነው፡፡ ይሄ መፅሐፍ ከበርካታ ዓመታት በፊት “ፍንጭ በሚል ርዕስ ወደ አማርኛ ተመልሶ ከአንባብያን በጎ ምላሽ አግኝቷል፡፡ አሁን ደግሞ ለሁለተኛ ጊዜ ታትሟል፡ ፡ ከበፊቱ የሚለየው የሽፋኑ በአዲስ መልክ መሰራት ነው” ብሏል ተርጓሚው፡፡ በጥልቅ የስለላ ስልት የተቀመረ ልብ አንጠልጣይ ታሪክ ያለው መፅሀፉ፤ በ375 ገፆች ተቀንብቦ፣ በ130 ብር ለገበያ ቀርቧል፡፡ “በ1945 ዓ.ም የሦስተኛው ራይክ ልጆች በዓለም ዙሪያ ተሸሽገው ነበር - እስከ 70ዎቹ ዓመታት፡፡ ማለትም በዕድሜ እስኪጎለምሱ ድረስ ሊቆዩ፡፡ በዛን ወቅትም እጅግ የረቀቀ ዕቅድና በስዊስ ባንክ የተቀመጠ 780 ሚሊዮን ዶላር ይጠብቃቸዋል፡፡ ዕቅዱን በተግባር ለመተርጎም የጉዳዩን ምስጢር የከፍተኛ
ናዚ ባለስልጣን ልጅ የሆነው አሜሪካዊው ኖኤል ሆልክሮፍት ነው፡፡ የሚያስደንቅ ሰነድ ማረጋገጫና በጠቅላላ ዓለምን ስጋት ላይ የሚጥል ይሆናል፡፡ ምን ይፈጠር ይሆን?” እያለ ይተርካል - ፍንጭ፡፡

Read 1865 times Last modified on Saturday, 02 September 2017 12:48