Sunday, 03 September 2017 00:00

“አብሱማ” መፅሀፍ ለንባብ በቃ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(10 votes)


      የደራሲ ታገል አምሳል “አብሱማ” ልብወለድ መጽሐፍ ለንባብ በቃ፡፡ መፅሀፉ በዋናነት በአፋር ክልል ስለሚካሄዱ፣ የሰርግ፣ የለቅሶ፣ የግርዛትና ተያያዥ ባህላዊ ክንውኖችና በተለይም በወቅታዊው የመልካም አስተዳደር እጦት ላይ የሚያጠነጥን እንደሆነ ደራሲው በማስታወሻው ገልጿል፡፡ በአፋር ስለሚከወን የወንድና የሴት ልጅ ግርዛት፣ ስለጋብቻና ለቅሶ ስነስርዓት የሚተርከው መፅሁፍ የተሰየመበት “አብሱማ” የተሰኘው ቃል፣ “ለጋብቻ የተመረጠ ጎሳ” ማለት እንደሆነም ተገልጿል፡፡ በ153 ገፅ የተመጠነው መፅሀፉ፣ በ51 ብር ከ50 ሳንቲም ለገበያ ቀርቧል፡፡

Read 6858 times