Print this page
Monday, 11 September 2017 00:00

የአማራና የትግራይ ክልል ወሰን አካለሉ

Written by  አለማየሁ አንበሴ
Rate this item
(14 votes)

 የአማራና የትግራይ ክልልን ሲያወዛግቡ ነበር  በተባሉት የፀገዴ እና የጠገዴ ወረዳዎች መካከል የድንበር ማካለል ስምምነት መፈጸሙ ተገለጸ፡፡ የሁለቱ ክልል ፕሬዚዳንቶች አቶ ገዱ አንዳርጋቸውና አቶ አባይ ወልዱ፤በጠገዴ ወረዳ በምትገኘው ቅርቃር ከተማ ተገኝተው ስምምነቱን  እንደፈጸሙ ታውቋል፡፡
በስምምነቱ መሰረት ለረጅም ዓመታት ሲያወዛግቡ ነበር የተባሉት በግጨው በረሃ የሚገኙት የማይሞቧ፣ሰላንዴ እና የአየር ማረፊያ፣ ሰፋፊ የእርሻና ኢንቨስትመንት ቦዎች ወደ አማራ ክልል ጠገዴ ወረዳ መከለላቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡ የትግርኛ ቋንቋ ተናጋሪዎች የሚበዙባቸው ሁለት የመኖሪያ መንደሮች ወደ ትግራይ ክልል፣ ፀገዴ ወረዳ መካለላቸው ተጠቁሟል፡፡ በሁለቱ የመኖሪያ መንደሮች ዙሪያ የሚገኙ የእርሻ መሬቶች በአማራ ክልል ስር እንዲካለሉ መወሰኑም ተገልጧል፡፡
ወደ አማራ ክልል በተካለሉ ቦታዎች የሚኖሩ የትግራይ ተወላጆች የሚያከናውኗቸው ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴዎች ሙሉ በሙሉ በአማራ ክልል ህግ እንዲተዳደሩም ከውሳኔ ላይ ተደርሷል ተብሏል፡፡

Read 5933 times