Saturday, 07 April 2012 09:17

“ግጥምን በጃዝ” ረቡዕ ይቀርባል

Written by  መልካሙ ተክሌ (melkamutekele@gmail.com)
Rate this item
(0 votes)

ወጣት የኪነጥበብ ባለሙያዎች የግጥም እና የሙዚቃ ሥራዎቻቸውን የሚያቀርቡበት “ግጥምን በጃዝ” ዘጠነኛ ወርሃዊ ዝግጅቱን በመጪው ረቡዕ ሜክሲኮ አደባባይ አካባቢ በሚገኘው ዋቢሸበሌ ሆቴል ይቀርባል፡፡ ከምሽቱ 12 ሰዓት ጀምሮ በሚቀርበው ዝግጅት ሜሮን ጌትነት፣ ቸርነት ወልደገብርኤል፣ ምስራቅ ተረፈ፣ በረከት በላይነህ፣ ሰለሞን ሳህለ እና ሌሎች የግጥም ሥራዎቻቸውን በጃዝ ሙዚቃ በመታጀብ የሚያቀርቡ ሲሆን የወግ ፀሐፊው በሃይሉ ገብረእግዚብሔር ወግ እንዲሁም የጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ሕክምና ዶክተሮች በድንገቴ ግብዣ እዚያው ግጥም በመግጠም በጃዝ አጅበው እንደሚያቀርቡም ይጠበቃል፡፡

 

 

Read 1120 times Last modified on Saturday, 07 April 2012 09:22