74ኛው ዙር ጦቢያ ግጥምን በጃዝ ምሽት የፊታችን ረቡዕ በራስ ሆቴል ይካሄዳል፡፡
በዕለቱ ገጣሚያኑ ነብይ መኮንን፣ ትዕግስት ማሞ፣ ምስራቅ ተረፈ፣ ዮሃንስ ገ/መድህን፣ መንግስቱ ዘገየ እና ሌሎችም ስራዎቻቸውን የሚያቀርቡ ሲሆን በመጋቢ ሀዲስ ሮዳስ ታደሰ ዲስኩር፣ አጭር ተውኔት ደግሞ በአርቲስት ሽመልስ አበራና በእታፈራሁ መብራቱ ለታዳሚ እንደሚቀር ታውቋል፡፡ መድረኩን ጋዜጠኛ ጌጡ ተመስገን ይመራዋልም ተብሏል፡፡