Print this page
Sunday, 10 September 2017 00:00

የሄለን በርሄ “እስኪ ልየው” አልበም ለአድማጭ ቀረበ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(1 Vote)

“ኦዛዛ አሌና” በተሰኘው ነጠላ ዜማዋና “ታስፈልገኛለህ” በተሰኘው ሙሉ አልበሟ እውቅናን ያገኘችው ድምፃዊት ሄለን በርሄ፣ “እስኪ ልየው” የተሰኘውን ሁለተኛ አልበሟን ከትላንት በስቲያ ሀሙስ ለገበያ አቀረበች፡፡ አልበሙ 14 ዘፈኖችን ያካተተ ሲሆን ሰርቶ ለማጠናቀቅ አምስት አመት እንደፈጀ ድምፃዊቷ ባለፈው ማክሰኞ በሰጠችው ጋዜጣዊ መግለጫ አስታውቃለች፡፡
በቅንብሩ ካሙዙ ካሳ፣ ዲልዶ ካሳ፣ ሚካኤል ሀይሉና ኩሩቤል ተስፋዬ የተሳተፉበት ሲሆን፣ በግጥምና ዜማ ኢዮቤል ብርሃኑ፣ ምዕራፍ አሰፋ፣ ዓለማየሁ ደመቀና ሌሎችም መሳተፋቸውን ተናግራለች፡፡ በቆሊያ ሲዲ አምራች ድርጅት በተመረተ ሲዲ የታተመው “እስኪ ልይህ” አልበም፤ በ40 ብር ለገበያ መቅረቡን የገለፀችው ድምፃዊቷ፤ አድናቂዎቿ አሪጂናሉን በመግዛት እንዲያዳምጡ ጥሪ አቅርባለች፡፡ ሄለን ከተባበሩት መንግስት ጋር በመተባበር፣ በሴቶችና ህፃናት መብትና መከበር ላይ አንድ ነጠላ ዜማ እንዳላትና ቪዲዮ ክሊፕ እንደተሰራላት ጨምራ ገልፃለች፡፡

Read 2922 times