Sunday, 10 September 2017 00:00

የዲጄ ሊ “እቴጌ” አልበም ለገበያ ቀረበ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(3 votes)

  በ97.1 ኤፍኤም ሬዲዩ “ሄሎ ሌዲስ” በተሰኘው ፕሮግራሟ በምታቀርባቸው ሙዚቃዎች የምትታወቀው ዲጄ ሊ እቴጌ “Black Note” የተሰኘ ሂፕ ሆፕ ስልት ያላቸውን ሙዚቃዎች ያካተተ አልበም ለአድማጭ አቀረበች፡፡ ተሰርቶ ለመጠናቀቅ ከአንድ ዓመት በላይ የወሰደውና በታዋቂው አቀናባሪ ሁን አንተ ሙሉ ተቀናብሮ፣ በፍሬ ጉጆ ኢንተርቴይመንት ፕሮዲዩስ የተደረገው አልበሙ፤ 14 በአገር፣ በፍቅር በሰላምና በተለያዩ ማህበራዊ ጉዳዮች ላይ የሚያጠነጥኑ ሙዚቃዎችን ማካተቱን ለማወቅ ተችሏል፡፡  ዲጄ ሊ በአገራችን በሂፕ ሆፕ ስልት የራሷን አልበም የሰራች የመጀመሪያዋ ሴት ዲጄ መሆኗም ተገልጿል፡፡ የአልበሙ መጠሪያ “እቴጌ” የተባለበት ምክንያት የአገራችንን ጀግና ሴቶች ለመወከል ሲሆን  “ብላክ ኖት” የሚለውም አገራችን የጥቁሮች ኩራት መሆኗን ለመግለፅና ኖት የሚለውም የሙዚቃ ኖታ ከሚለው የተወሰደ መሆኑን አቀናባሪ ሁን አንተ ሙሉ በመግለጫው ላይ ተናግሯል፡፡

Read 2238 times