Sunday, 17 September 2017 00:00

ለሁለተኛ ጊዜ በ”ቆሼ” በደረሰው አደጋ አንድ ሰው ሞተ

Written by  አለማየሁ አንበሴ
Rate this item
(6 votes)

“ተጨማሪ አደጋ እንዳይደርስ አካባቢው
በአደጋ ቀጠናነት መታጠር አለበት”

በአዲስ አበባ በተለምዶ “ቆሼ” ተብሎ በሚጠራው ቦታ፣ ከትላንት በስቲያ ሐሙስ፣ከቀኑ 6፡15 ላይ በድጋሚ በደረሰ የቆሻሻ መደርመስ አደጋ፣ የአንድ ሰው ህይወት ማለፉን የአዲስ አበባ እሣትና ድንገተኛ አደጋዎች መቆጣጠርና መከላከል ኮሚሽን፣ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ ለአዲስ አድማስ ገልጸዋል፡፡   
አደጋው ያጋጠመው በአካባቢው በቆሻሻ መልቀም ስራ ላይ በተሰማሩ ሁለት ወጣቶች ላይ ሲሆን አንደኛው ከናዳው ሮጦ ሲያመልጥ፣ሌላኛው ማምለጥ ሳይችል ቀርቶ ህይወቱ ማለፉንና አስክሬኑም በቁፋሮ መውጣቱን አቶ ንጋቱ አስረድተዋል፡፡
አደጋው የደረሰው ባለፈው ዓመት፣ከ115 በላይ ዜጎችን በጨረሰው ቦታ ላይ መሆኑን የጠቆሙት የህዝብ ግንኙነት ባለሙያው፤ከአካባቢው ነዋሪዎች እንዲነሱ የተደረገ ቢሆንም አካባቢው በአደጋ ቀጠናነት ባለመታጠሩ አደጋ እየፈጠረ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ተጨማሪ አደጋ እንዳይደርስም የቆሻሻ ቦታው መታጠርና ሰዎች ወደ አካባቢው እንዳይጠጉ የማድረግ የጥንቃቄ ስራ መሰራት እንዳለበትም አሳስበዋል፡፡

Read 2758 times