Print this page
Saturday, 30 September 2017 14:58

“አመፀኛው ክልስ” ወደ ፊልም ተቀየረ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(6 votes)

   ከደች አባትና ኢትዮጵያዊት እናት የተወለደው የዳንኤል ሁክ፣ “አመፀኛው ክልስ” የተሰኘው መፅሐፍ፣“The Bastard” በሚል ወደ ፊልም በእንግሊዝኛ ተቀየረ፡፡ በእንግሊዝኛ ቋንቋ ተሰርቶ ለአለም ህዝብ እንዲቀርብ ያደረጉት የደች የፊልም ባለሙያዎች መሆናቸውን የፊልሙ ፕሮሞሽን የኢትዮጵያ ተወካይ ጋዜጠኛ በፍቃዱ አባይ ገልጿል፡፡የ1፡38 ርዝመት ባለው በዚህ ፊልም ላይ ባለታሪኩ ዳንኤል ሁክ እንደተወነ ለማወቅ ተችሏል፡፡ የመፅሐፉ ታሪክ ከሁለት አገር ዜጎች የተወለደው ዳንኤል ሁክ፤ ክልስነቱን ተከትሎ በማህበረሰቡ የደረሰበትን
መገለልና በወላጅ አባቱ የተፈፀመበትን ክህደት በመቃወም እስከ ሞት ስላስፈረደበት የወንጀል ድርጊት ይተርካል፡፡ ቀደም ሲል “Divergent Nederlands” እና “The forgotten Nether lands` በሚሉ ርዕሶች ተተርጉሞ መቅረቡ ታውቋል፡፡

Read 1993 times