Saturday, 30 September 2017 14:56

የሙሉጌታ ሉሌ “በዕዳ የተያዘ ህዝብ” ለንባብ በቃ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(2 votes)

የታዋቂው ጋዜጠኛና የፖለቲካ ተንታኝ ሙሉጌታ ሉሌ የተመረጡ መጣጥፎችን ያካተተው “በዕዳ የተያዘ ህዝብ” የተሰኘ መፅሐፍ ሰሞኑን ለንባብ በቃ።መፅሐፉ ጋዜጠኛው ለግማሽ ክፍለ ዘመን ያህል ከፃፋቸው እጅግ በርካታ መጣጥፎች በልጁ ኤዶም ሙሉጌታ ሉሌ ተመርጦ የታተመ መሆኑም ተገልጿል።ህዝቡ በምን ዕዳ ነው የተያዘው? በገንዘብ፣ በግፍ፣ባልተመለሱ ጥያቄዎች ወይስ? የሚለውን መፅሐፉ
ይተነትናል ተብሏል፡፡ በ339 ገፆች የተቀነበበው መፅሐፉ በ81 ብር እና በ25 ዶላር ለገበያ ቀርቧል። ከዚህ ቀደም የጋዜጠኛው መጣጥፎች ስብስብ
ያሉበት “ሰው ስንፈልግ ባጀን” የሚል መፅሃፍ ለንባብ መብቃቱ ይታወሳል፡

Read 1142 times