የሰባት ወጣት ሰዓሊያን ከ35 በላይ ስራዎች የተካተቱበት “ህብር 6” የስዕል አውደ ርዕይ፣ ባለፈው ሰኞ ቦሌ ኤድናሞል ፊት ለፊት በሚገኘው ትሪኒቲ ሆቴል ተከፈተ፡፡ አውደርዕይው የተዘጋጀው በኤፍሬም አርት ስቱዲዮ ጋለሪ ሲሆን ስዕሎቹ በአብስትራክትና ሪያሊስቲክ የአሳሳል ዘይቤ የተሳሉ ናቸው ተብሏል።ከዚህ ቀደም “ህብር” በሚል ስያሜ አምስት የስዕል አውደርዕዮችን እንዳዘጋጁ የጠቆሙት የስቱዲዮውና
ጋላሪው መስራች አቶ ኤፍሬም፤ “ህብር 6” እስከ ፊታችን ሐሙስ ድረስ ለተመልካች ክፍት ሆኖ ይቆያል ብለዋል፡፡