“በአራጣ የተያዘ ጭን” በተሰኘው የመጀመሪያ መፅሐፉ የሚታወቀው የደራሲ ዮፍታሔ ካሳ አጫጭር ታሪኮችንና ወጎችን ያካተተው “የሚስት መዋጮና ሌሎችም” የተሰኘ አዲስ መፅሐፍ በገበያ ላይ ዋለ፡፡ በማህበራዊ ጉዳይ፣ በፍልስፍና፣ በስነ - ልቦና፣በፍቅርና ሌሎች ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ ከ28 በላይ አጫጭር ታሪኮችንና ወጎችን ያካተተው መፅሐፍ፤ በ212 ገፆች ተቀንብቦ፣ በ61 ብር ከ20 ሳንቲም ለገበያ ቀርቧል፡፡