Saturday, 30 September 2017 15:14

የሙሴቬኒን ስልጣን የሚያራዝመው ዕቅድ የፓርላማ አባላትን አደባደበ

Written by 
Rate this item
(0 votes)

የኡጋንዳውን ፕሬዚዳንት ዮሪ ሙሴቬኒን የስልጣን ዘመን ያራዝማል የተባለው አወዛጋቢ የህገ መንግስት ማሻሻያ፣ ባለፈው ማክሰኞ የአገሪቱን ፓርላማ አባላት ማጋጨቱንና ማደባደቡን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡
ፕሬዚዳንት ሙሴቬኒ ተጨማሪ አንድ የስልጣን ዘመን በመንበራቸው ላይ እንዲቆዩ ለማድረግ በቀረበው ምክረ ሃሳብ ላይ የፓርላማው አባላት ክርክር ለማድረግ ቀጠሮ ቢይዙም፣ ጉዳዩ ባለፈው ማክሰኞ የፓርላማ አባላትን ቡጢ ማሰናዘሩንና በወንበር እስከመደባደብ ማድረሱን ዘገባው ገልጧል፡፡ የፓርላማው ስብሰባ ከመጀመሩ በፊት የፕሬዚዳንቱን ስልጣን መራዘም በመቃወም ተማሪዎችና የፖለቲካ አራማጆች አደባባይ ወጥተው ተቃውሟቸውን በሚያሰሙበት ወቅት፣ ፖሊስ በአስለቃሽ ጭስ እንደበተናቸው የጠቆመው ዘገባው፤ የፓርላማ አባላቱ እርስ በእርስ ሲቧቀሱ፣ በአገሪቱ የቴሌቪዥን ጣቢያ መታየቱንም አመልክቷል፡፡
ታዋቂው የአገሪቱ የተቃዋሚ ፓርቲ አመራር ኪዛ ቤሲጄ፣ ተቃዋሚዎችን በማደራጀት፣ ወደ ፓርላማው ለተቃውሞ በማምራት ላይ ሳሉ በፖሊስ ቁጥጥር ስር መዋላቸውን የአገሪቱ ፖሊስ ቃል አቀባይ መናገራቸውንም ዘገባው አክሎ ገልጧል፡፡

Read 3441 times