Print this page
Saturday, 14 October 2017 15:50

“ከማእከላዊ እስከ ቂሊንጦ” መጽሐፍ ለገበያ ቀረበ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(6 votes)

በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ምክንያት በርካታ ማተሚያ ቤቶች ረቂቁን ለማተም ፍቃደኛ ሳይሆኑ በመቅረታቸው ከ6 ወራት በላይ ለገበያ ሳይቀርብ የቆየው የጋዜጠኛ ሰለሞን ከበደ “ከማዕከላዊ እስከ ቂሊንጦ” የተሰኘ ሰሞኑን ለአንባቢ ቀርቧል፡፡ አሳታሚም አታሚም ለማግኘት ከፍተኛ ፈተና ኾኖበት እንደነበር የሚገልጸው ጋዜጠኛ ሰለሞን ከበደ፤ መጽሐፉ መውጣት ከነበረበት ጊዜ በ6 ወራት የዘገየው በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁና ይህንኑ ተከትሎ በማተሚያ ቤቶች አካባቢ በተፈጠረ “የተጋነነ ፍርሃት” እንደነበር ይናገራል። በኢስላማዊ ጉዳዮች የምታተኩረው “የሙስሊሞች ጉዳይ” መጽሔት ማኔጂንግ ኤዲተር የነበረው አቶ ሰለሞን፤ የሽብር ክስ ተመስርቶበት በማእከላዊ፣ ቃሊቲና ቂሊንጦ 3 ዓመት ከ3 ወራት እና
ከአንድ ቀን በድምሩ 456 ቀናትን አሳልፏል፡፡ በነዚህ የእስር ጊዜያት በማረሚያ ቤቶች የታዘባቸውን አንኳር ጉዳዮች በመጽሐፉ ውስጥ ማካተቱን ይናገራል፡፡ 147 ገጾች ያሉት ይህ መጽሐፍ፤ ለመጀመሪያ ኅትመት 5 ሺ ቅጂዎች የተባዙ ሲሆን በሊትማን መጻሕፍት አሳታሚነት ለንባብ በ49 ብር ቀርቧል፡፡

Read 4132 times