Tuesday, 17 October 2017 10:43

ሜታ ቢራ 50ኛ ዓመቱን እያከበረ ነው

Written by  መታሰቢያ ካሳዬ
Rate this item
(2 votes)

 አዲሱን ባለ 500 ሚሊ ሊትር የቢራ ጠርሙስ ይፋ አድርጓል
                             
      የዲያጅዮ ኩባንያ አካል የሆነው ሜታ አቦ ቢራ ፋብሪካ የተመሰረተበትንና የኢትዮጵያን የቢራ ገበያ የተቀላቀለበትን 50ኛ ዓመት የወርቅ ኢዮቤልዩ በዓል እያከበረ ነው፡፡ ፋብሪካው አዲሱንና 500 ሚሊ ሊትር የሚይዘውን የሜታ ቢራ ጠርሙስ ከትናንት በስቲያ ይፋ አድርጓል፡፡
በ1959 ዓ.ም የተቋቋመው ይኸው ፋብሪካ፣ ሰሞኑን ይፋ ያደረገው አዲሱ የቢራ ማሸጊያ ጠርሙስ፤ በቀላሉ ሊለይ የሚችልና የሜታ ቢራ ነባር መለያ የሆኑትን ቀይና ወርቃማ ቀለማትን የያዘ፣ በምርት ሽያጩ ላይ የራሱን ከፍተኛ ሚና ይጫወታል ተብሎ የታመነበት እንደሆነም ተገልጿል፡፡ የሜታ ቢራ ብራንድ ማናጀር አቶ ብሩክ በላይ በሥነ ስርዓቱ ላይ እንደተናገሩት፤ ፋብሪካው የጥንት መነሻውንና ማንነቱን በሚያከብር፣ የቀደመውን ጣዕምና ክብሩን ጠብቆ በአዲስ አስተሻሸግ ለደንበኞቹ ቀርቧል፡፡ ደንበኞቹ ቀደም ሲል ከቢራው የሚያገኙትን እርካታና ጣዕም በአዲሱ የቢራ ጠርሙስም ያገኙታል ሲሉ ተናግረዋል፡፡  
ሜታ አቦ ቢራ ፋብሪካ በ1959 ዓ.ም ሲቋቋም፣ በቀን 50 ሺ ሄክቶ ሊትር ቢራ የማምረት አቅም የነበረው ሲሆን ለ128 ሰራተኞች የሥራ ዕድል ከፍቶ ነበር፡፡
እ.ኤ.አ በጥር ወር 2012 ዓ.ም ዲያጅዮ ኩባንያ፣ ሜታ አቦ ቢራ ፋብሪካን በ225 ሚሊዮን ዶላር በመግዛት የኩባንያው አካል አድርጎታል፡፡ ከ119 ሚሊዮን ዶላር በላይ የሆነ ውጪ በማድረግም የማስፋፊያ ስራዎች መሠራታቸው ተገልጿል፡፡ ሜታ ቢራ በአሁኑ ወቅት ክላሲክ፣ ማልታ ጊነስ ጊነስ ፎርኒ ኤክስታራ ስታውት፣ ኩሩ ማልት፣ አዝመራ ቢራ አዝመራ ድራፍትና ሜታ ድራፍትን በማምረት ለደንበኞቹ እያቀረበ ይገኛል፡፡

Read 3730 times