Print this page
Saturday, 21 October 2017 13:43

155 ሚ. የዓለማችን ህጻናት የመቀንጨር ችግር ተጠቂ ናቸው

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(5 votes)

   ”ዋሽ ኢትዮጵያ ሙቭመንት” የሩብ ዓመቱን የልምድ ልውውጥ አካሄደ
                 
    የኢትዮጵያ የውሃ፣ የአካባቢ ንፅህና እና የስነ-ጤና አጠባበቅ እንቅስቃሴ (WASH Ethiopia Movement) በየሩብ አመቱ የሚያዘጋጀውን የልምድ ልውውጥና የተሞክሮ የውይይት መድረኩን ሰሞኑን ያካሄደ ሲሆን፣ ኢትዮጵያን ጨምሮ 10 አገራት የውሃ፣ የአካባቢ ንጽህናና እና የስነ-ጤና አጠባበቅን ከስርዓተ ምግብ ጋር በማቀናጀት ረገድ ያሉባቸውን ክፍተቶች የሚያመላክት አዲስ የጥናት ሪፖርት ይፋ ተደርጓል፡፡
“የውሃ፣ የአካባቢ ንጽህናና የስነ-ጤና አጠባበቅን ከስርዓተ ምግብ ጋር ማቀናጀት” በሚል ርዕሰ ጉዳይ ላይ ባተኮረውና ባለፈው ማክሰኞ በሀርመኒ ሆቴል በተካሄደው የዋሽ ኢትዮጵያ ሙቭመንት የልምድ ልውውጥ መድረክ ላይ፣ የጤና ጥበቃና የትምህርት ሚኒስቴር እንዲሁም በሁለቱም ዘርፎች የተሰማሩ የተሰማሩ ከ50 በላይ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ተወካዮች የተሳተፉ ሲሆን፣ በቀረቡ የተመረጡ ተሞክሮዎች ላይ ተወያይተው፣ በቀጣይም በአገሪቱ የሚታየውን የስርዓተ ምግብ ችግር ለመቀነስ በሚደረገው ጥረት የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ማበርከት በሚችሉበት ሁኔታ ላይ መክረዋል፡፡
በኢትዮጵያ በውሃ፣ የአካባቢ ንጽህናና የስነ-ጤና አጠባበቅ እና በስርዓተ ምግብ ዙሪያ የሚወጡ እቅዶችን የበለጠ አስተሳስሮና አቀናጅቶ ማስኬድ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ የመከሩት ተሳታፊዎቹ፤ የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ባዘጋጀው አዲሱ ቤቢ ዋሽ ጋይድላይን ዙሪያም ተወያይተዋል፡፡
በኢትዮጵያ ላለፉት 30 ዓመታት ትኩረቱን በንጹህ የመጠጥ ውሃ፣ በአካባቢ ንፅህናና በስነ-ጤና አጠባበቅ ላይ አድርጎ ሲሰራ የቆየው ዋተር ኤድ፣ ከአክሽን አጌንስት ሀንገርና ከሼር ኮንስቲም ጋር በመተባበር የሰራውና በ10 አገሮች ላይ የፖሊሲ ትንተና የሚያደርገው “The Recipe for Success” የተሰኘ አዲስ የጋራ ጥናት ሪፖርት በመድረኩ ላይ ይፋ የተደረገ ሲሆን፣ የአገራት መንግስታት፤ ፖሊሲ አውጭዎች፣ በዘርፎቹ  የተሰማሩ ተቋማትና ለጋሾች የንጹህ የመጠጥ ውሃ፣ የአካባቢ ንፅህናና የስነ-ጤና አጠባበቅን ከስርዓተ ምግብ ጋር በምን መልኩ አስተሳስረው ውጤታማ የድርጊት መርሃ ግብሮችንና ፕሮግራሞችን መቅረጽ እንደሚችሉም አመልክቷል፡፡
በዓለማችን ከአምስት ዓመት በታች ዕድሜ ያላቸው 155 ሚሊዮን ህፃናት፣ ከጽንሰት አንስቶ ባሉት የመጀመሪያዎቹ 1 ሺህ ቀናት ተገቢውን የተመጣጠነ ምግብ ካለማግኘት ጋር ተያይዞ የሚከሰት የመቀንጨር ችግር ተጠቂ መሆናቸውን የጠቆመው ሪፖርቱ፤ ህጻናትን ለመቀንጨር ችግር የሚያጋልጠው ሌላው ቀዳሚ መንስኤ ደግሞ የአካባቢ ንጽህና አለመጠበቅ መሆኑን በመግለጽ፣ የውሃ የአካባቢ ንፅህናና የስነ-ጤና አጠባበቅን ከስርዓት ምግብ ጋር አቀናጅቶ መስራት እንደሚገባ አስምሮበታል፡፡
844 ሚሊዮን የአለማችን ህዝቦች የንጹህ የመጠጥ ውሃ አቅርቦት ተጠቃሚ እንዳልሆኑና 4.5 ቢሊዮን ያህል ሰዎችም አግባብነት ያለው የአካባቢ ንጽህና አገልግሎት እንደማያገኙም ጥናቱን ያቀረቡት የዋተርኤይድ ኢትዮጵያ ካንትሪ ዳይሬክተር ቤለትሄም መንግስቱ አመልክተዋል፡፡
በጤና ጥበቃ ሚኒስቴር የሰቆጣ ስምምነት (ቃልኪዳን) ማስፈፀሚያ ክፍል ሀላፊ የሆኑት ዶ/ር ሲሳይ ሲናም በበኩላቸው፣ የመቀንጨር ችግር

Read 6543 times