Saturday, 21 October 2017 13:54

“ወቅቶች” (Seasons) የስዕል ኤግዚቢሽን ተከፈተ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)

   የሰዓሊ ኑሩ አበጋዝ  ስራዎች ለእይታ የቀረቡበት “ወቅቶች”(Seasons) የተሰኘ የስዕል ኤግዚቢሽን ትላንት ምሽት ላፍቶ ሞል በሚገኘው ላፍቶ አርት ጋለሪ ተከፈተ፡፡ ሰዓሊው የብቻ ኤግዚቢሽን ሲያዘጋጅ የአሁኑ ለ7ኛ ጊዜ ሲሆን ከ60 በላይ ስዕሎች ለእይታ ማቅረቡ ታውቋል፡፡ የኤግዚቢሽኑ ስያሜ “ወቅቶች” የተባለውም በተለያዩ ወቅቶች የተለያዩ ሀሳቦች በስዕሉ ስለተንፀባረቁ መሆኑን ሰዓሊው ተናግሯል። ለአንድ ወር ለተመልካች ክፍት ሆኖ በሚቆየው በዚህ ኤግዚቢሽን ላይ የቀረቡት ስዕሎች፣ አብዛኞቹ ቀለም ቅቦች ሲሆኑ በናስትሮ ፕላስተር የተሰሩም እንደሚገኙበት ታውቋል፡፡  
ሰዓሊ ኑሩ ከዚህ ቀደም በአሊያንስ ኢትዮ ፍራንሴዝ፣ በአስኒ ጋለሪና በጀርመን የባህል ተቋም ስራዎቹን ለእይታ ያበቃ ሲሆን በውጭ አገራት ደግሞ በፈረንሳይ፣ ዱባይ፣ ካሜሩን፣ ጅቡቲና በሌሎች አገራት ስዕሎቹን ማቅረቡን ጠቁሞ፣ ከ40 በላይ የቡድን የስዕል ኤግዚቢሽኖች ላይ መሳተፉንም ጨምሮ ገልጿል፡፡

Read 2026 times