Saturday, 21 October 2017 14:03

“እስረኛው” ረዥም ልብ ወለድ ዛሬ በወንጂ ይመረቃል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)

      በአቶ ሰለሞን ገ/ጊዮርጊስ እውነተኛ ታሪክ ላይ ተመስርቶ የተጻፈው “እስረኛው” የተሰኘ የረዥም ልብ ወለድ መፅሐፍ፤በዛሬው ዕለት ከቀኑ 8፡00 ጀምሮ በወንጂ ስኳር ፋብሪካ አዳራሽ ይመረቃል። የመጽሐፉን ታሪክ ጸሐፊው በ1971 ዓ.ም በወህኒ ቤት በእስር ላይ ሳሉ እንደጀመሩትና በቅርቡ ተጠናቆ፣ለህትመት ብርሃን መብቃቱን ለማወቅ ተችሏል፡፡ በምረቃ ሥነ ስርዓቱ ላይ አቶ አላምረው ዳኜ በመፅሐፉ ላይ ዳሰሳ የሚያቀርቡ ሲሆን የተለያዩ የሥነ ፅሁፍ ባለሙያዎች፣ስራዎቻቸውን ለታዳሚው ያቀርባሉ ተብሏል፡፡ በ236 ገጾች የተቀነበበው መፅሐፉ፤ በ65 ብር ለገበያ ቀርቧል፡፡
ደራሲው  አብዮቱ ከፈነዳ በኋላ ለእድገት በህብረት ዘመቻ ዘምተው፣ ደርግን በመቃወም ከተመለሱ በኋላ በነበራቸው የፖለቲካ ተሳትፎ በአባድር/መተሀራ እስር ቤት ታስረው እንዲገደሉ ከተፈረደባቸው እስረኞች አንዱ የነበሩ ሲሆን ከሞት ተርፈው በ1977 ዓ.ም ከእስር መለቀቃቸው ታውቋል። ደራሲ ሰለሞን ገ/ጊዮርጊስ፣ከዚህ ቀደም “The Return of Odessa’s” የተሰኘውን የሆሜር መፅሐፍ “ኦዲሲየስ ከርታታው ንጉስ” በሚል ርዕስ ተርጉመው ለንባብ ማብቃታቸው ይታወሳል፡፡   

Read 2480 times