Print this page
Saturday, 28 October 2017 10:42

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከአፍሪካ ቀዳሚ የሚያደርገውን ቦይንግ 787-9 ድሪም ላይነር አውሮፕላን ተረከበ

Written by  አለማየሁ አንበሴ
Rate this item
(0 votes)

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከአፍሪካ ቀዳሚ የሚያደርገውን ቦይንግ 787-9 ድሪም ላይነር አውሮፕላን ትናንት (አርብ) ከቦይንግ ኩባንያ ተረክቦ፣ ወደ ሀገር ውስጥ ያስገባ ሲሆን የዚህ ዘመናዊ አውሮፕላን ባለቤት በመሆን በአለም ከጃፓን ቀጥሎ ኢትዮጵያ ሁለተኛዋ መሆኗ ታውቋል፡፡
ቦይንግ 787-9 ድሪም ላይነር አውሮፕላን አለም ላይ የመጨረሻው የአቪዬሽን ቴክኖሎጂን ያካተተ እንዲሁም ከመደበኛ አውሮፕላኖች በተለየ የነዳጅ ፍጆታው 20 በመቶ መቆጠብ የሚችል መሆኑ ታውቋል፡፡ አውሮፕላኑ ከውጪ የሞተር ድምፅ የማያስገባ፣ ጣራው ከሌሎች አውሮፕላኖች ከፍ ያለ እና 315 ተሳፋሪዎች የሚያስተናግዱ ምቹ ወንበሮችን ያካተተ መሆኑን ተገልጿል፡፡
አየር መንገዱ ከዚህ ቀደም ከአፍሪካ ቀዳሚ ያደረገውን ቦይንግ 787-8 ድሪም ላይነር በስራ ላይ ማዋሉን የጠቆሙት የአየር መንገዱ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ተወልደ ገ/ማርያም፤ “አዲሱ ቦይንግና 787-9 ድሪም ላይነር አውሮፕላንም አየር መንገዱን በአቪዬሽን ቴክኖሎጂ ከአፍሪካ ሀገራት መሪ ያደርገዋል፤ የአገልግሎት ጥራታችንንም ለመጨመር ያስችለናል” ብለዋል፡፡ የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአሁኑ ወቅት ወደ መቶ አለማቀፍ መዳረሻዎች በረራ የሚያደርግባቸው ዘመናዊዎቹን 20 ቦይንግ 787 ድሪም ላይነር አውሮፕላኖችን ጨምሮ 93 አውሮፕላኖች እንዳሉት ተገልጿል፡፡

Read 2728 times