Print this page
Saturday, 04 November 2017 11:42

የቡና የግብርናና የላይቭ ስቶክ ኤግዚቢሽን ይከፈታል

Written by  አለማየሁ አንበሴ
Rate this item
(1 Vote)

 የተለያዩ ሁነቶችንና የንግድ ትርኢቶችን በማዘጋጀት የሚታወቀው “ፋልከን ማርኬቲንግና ፕሮሞሽን”፤ ከህዳር 8 እስከ 10 ቀን 2010 ዓ.ም የሚቆይ የቡና፣ የግብርናና የላይቭ ስቶክ ኤግዚቢሽን ሊከፍት ነው፡፡ በአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማዕከል በሚከፈተው በዚህ ኤግዚቢሽን ላይ ከመቶ በላይ የውጭና የአገር ውስጥ ነጋዴዎች፣ አምራቾች፣ ኤክስፖርት አድራጊዎችና የዘርፉ አማካሪዎች እንደሚሳተፉ አዘጋጆቹ ባለፈው ሳምንት በሞዛይክ ሆቴል በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ አስታውቀዋል፡፡
ለሦስት ቀናት በሚቆየው በዚህ ኤግዚቢሽን ላይ ተሳታፊዎች፤ ምርትና አገልግሎታቸውን ለጎብኚዎች ከማስተዋወቅም ባለፈ ናሙና የሚያቀርቡ ሲሆን በተለይ በቡና ዘርፍ የተሰማሩ ነጋዴዎች፣ ምርታቸውን ለጎብኚዎች ያስቀምሳሉ ተብሏል፡፡
ከኤግዚቢሽኑ ጎን ለጎን፣ ነጋዴዎች የእርስ በእርስ የቢዝነስ ትስስር በሚፈጥሩበት መንገድ ላይ ውይይትና ምክክር እንደሚያደርጉ ተነግሯል፡፡ ኤግዚቢሽኑን በርካታ ሰው ይጎበኘዋል ተብሎ እንደሚጠበቅ የፋልከን ኃላፊዎች ተናግረዋል፡፡   

Read 1674 times