Saturday, 04 November 2017 11:46

“ደመኞች” ዛሬ ይመረቃል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)

    የካፕቴን አልአዛር አያሌው ሁለተኛ ስራ የሆነው “ደመኞች” የተሰኘ ታሪክ ቀመስ ረጅም ልብ ወለድ መፅሀፍ ዛሬ ከቀኑ 8፡00 ጀምሮ መገናኛ አካባቢ በሚገኘው አፈረንሲስ ኢንተርናሽናል ሆቴል በተለያዩ ኪነ-ጥበባዊ ዝግጅቶች ታጅቦ ይመረቃል፡፡
ከግማሽ ምዕተ ዓመት በላይ ያስቆጠረን ታሪክ መሰረት አድርጎ ከታሪኩ አወቃቀር እስከ ፍፃሜው የብዙኃኑን ኢትዮጵያዊ የህይወት ውጣ ውረዳ ያስቃኛል የተባለው መፅሀፉ፤ በክፍል 1 የተንጠለጠለውን ታሪክ መቋጫ ክፍል ሁለት ሆኖ መቅረቡን ደራሲው በመግቢያቸው አስፍረዋል፡፡ ካፒቴኑ ከዚህ ቀደም “የተሰረቀው ህልም” የተሰኘውን ክፍል አንድ መፅሀፍ ለንባብ ማብቃታቸው የሚታወስ ሲሆን ቀደም ሲል የቀድሞው አየር ሀይል ባልደረባ በመሆን በመምህርነትና በውትድርና አገራቸውን አገልግለዋል፡፡ “ደመኞች” የተሰኘው መፅሀፍ በ250 ገፆች ተመጥኖ፣ በ100 ብር ለገበያ ቀርቧል፡፡

Read 774 times