Monday, 13 November 2017 09:57

የስውሮቹ ታሪኮች መምጣት

Written by  ቢኒያም ዓሊ
Rate this item
(1 Vote)

 “ታሪክ ለህዝብ እንጂ ለባለታሪኮች አይፃፍም”
           
   የስውሮቹ ታሪኮች መምጣት
“ታሪክ ለህዝብ እንጂ ለባለታሪኮች አይፃፍም”
ኘሮፌሰር ፍቅሬ ቶሎሳ፤ በአዲሱ መፅሀፋቸው ስውር እና ያልተነገረ ታሪክ ይዘው መጥተዋል። እስከዘመናችን ድረስ ለህዝብ ይቀርቡ ከነበሩ የኢትዮጵያ ታሪኮችና ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ተደብቀው የነበሩት ከታተሙበት ጊዜ ወዲህ ስላለው አንፃራዊ ልዩነት፣ ከታሪክ አንባቢ እይታ አንፃር ስለመፅሀፉ መጠነኛ ዳሰሳ አደርጋለሁ።
ታሪክ ያለፈ ጊዜ እውነታ የሚገለፅበት የሥነፅሁፍ ዘርፍ ሲሆን እንደ ፀሃፊው እውቀትና ምንጩ፣ እንደአስፃፊውም ማንነት ጭምር እንደሚለያይ ይታወቃል። የአንድ ግለሰብን ወይም የአንድ ቤተሰብን ታሪክ በምሳሌነት ብናነሳ፣ ከወላጅና ቤተሰቡ በበለጠ በሌሎች ሰዎች እንደማይታወቅ አባቶቻችን በተረት ጭምር ትተውልናል፦ ”ከራስ በላይ…””ለባለቤቱ…””ያለባለቤቱ…”ወዘተ።ታዲያ የዚህ ቤተሰብ ታሪክ እንደፍላጎታቸውና ማንነታቸው ይለያል። ደርሶት የሚያነብበው ቀጣይ ትውልዳቸው ወይም ቤተሰብ ያልሆነ፣ ስለእነርሱ እንዲታወቅ የሚፃፍለት በመሆኑ ወገንተኝነት ያጠላዋል ሊያስብል ይችላል።ነገር ግን በእነርሱ የቀረበውን ውድቅ የሚያደርግ የማንም ወገን በወቅቱ የፃፈው ባይሆንም ሌላ ማረጋገጫ እስካልተገኘ ድረስ ተቀባይነት ይኖረዋል። ለእውነታው ቢያንስ ቅርብ በመሆኑ፣ የታሪክ ፀሃፊዎቹ ልጆቻቸውም ሆንን ሌላው ወገን፣ በመግባባትና በማረጋገጥ ልንጠቀምበት ይገባል።
በሌላ መልኩ የዚህን ቤተሰብ ሆነ ህዝብ ታሪክ ለአፈታሪክነት ሳይበቃ በጊዜው እንደተከሰተ እየጠየቀ፣ በገለልተኝነትየሚፅፍወገንነበረ።
ይህ ወገን ታሪክ እንደነበረ ለመናገር ተፅእኖ ባይኖርበትም የታሪክ ክስተቶች የሚፈፀሙበትን እውነተኛ ምክንያት ሁሌ አያውቅም። የተነገረን፣ ያጣራውንና በጊዜው የተሰራውን አሉባልታ ጭምር (የእረኛ ምን አለን) የሁሉ ወገን አመለካከትን ጨምሮ የመፃፍ እድል አለው። ይህን የሚያደርጉ ታሪኩን ለልጆቻቸው በማስተማር ቢያስተላልፉትም የታሪኩ ጠቃሽ የሆኑት ቤተሰቦችም ሆኑ ህዝቡ ግን ለመቀበል ሲቸገር ይታያል።
በሀገራችን ምድር ድምፅን በፊደል ማስነበብ ከታወቀና 7ኛ ትውልድ በሆነው ሄኖክ በመፅሃፍ ከሰፈረ ወዲህ ስነ-ፅሁፍን በመጠቀም እስከ ኖህድረስና ከኖህ በኋላም በነገሱት ልጆቹ ጭምር ታሪኩ ሲፃፍ ቆይቷል። ከ3ሺህ አመታት አንድነት በኋላ ቋንቋ ሲለያይና አንድ ግለሰብ ከቤተሰቡ ውጭ መግባባት ሲያቅተው፣ የሚግባባውን የራሱን ቤተሰብ ብቻ ይዞ እስከተለያየባት ቀን ድረስ የአለም ህዝብ ታሪክ ይግባባበት በነበረው አሁንም ባለው በሱባ ቋንቋ ሲፃፍ ቆይቷል። በዚህ መለያየትና ተከታትለውም በመጡ ታሪካዊ ግጭቶች ሳቢያ፣ ታሪክ መዝጋቢዎች ለብቻቸው ተለይተው ለመኖርና እውነታውን በተቻላቸው መጠን በፅሁፍ ለማስፈር ችለዋል ወይም ተገድደዋል። እነዚህ የታሪክ መዝጋቢዎች እንደማንኛውም የስልጣን ሹመት መሪራስ በሚል የማእረግ ስም እየተጠሩ ኃላፊነታቸውን ተወጥተዋል። ከትውልድ ወደ ትውልድ የሚተላለፈውን የአባቶቻችንን ትላልቅና ትናንሽ ታሪካዊ ስራዎችን ጨምረው አስፍረውልን አልፈዋል።
የዘመናችን ታሪክ ያዥ የነበሩትና በቅርብ ከዚህ አለም የተለዩን መሪራስ አማን፣ በላይ ከጥንት ጀምሮ በተለያዩ ቋንቋዎች ተጽፈው የነበሩትን ወደ አማርኛ ተርጉመው፣ ከ24 መጻህፍት በላይ አዘጋጅተዋል፤ ከነዚህም መካከል 15ቱ ለህትመት እንዲበቁ አድርገዋል፤ የሌሎቹምህትመትይቀጥላልተብሏል።
መሪራስ አማን በላይ፣ ከሱዳንዋጀበል ኑባ ካገኙዋቸው እነዚህ የጥንት ታሪካዊ ሠነዶች መካከል በጥሩ ይዞታ ላይ የነበረ አንድ መፅሃፍ ከዓመታት በፊት በሸገር ሬዲዮ በጋዜጠኛነት ስሰራ አይቼአለሁ። እርሳቸውንም ለአጭር ጊዜ  ለማነጋገር መቻሌን በዚህ አጋጣሚ ለማረጋገጥ እወድዳለሁ።ይዘውት የነበረውን መፅሃፍ ዕድሜ፣ በአይኔ አይቼ ለመናገር ባልችልም፣ ሃሳቡ ተቀባይነት ቢኖረውም እንኳን በርግጠኝነት መናገር የሚቻለው፣ ያ ጥራዝ ከሌላ ካረጀ ብራና ላይ መቼ እንደተገለበጠ ብቻ ነው።በፕሮፌሰሩ ፍቅሬ ቶሎሳ እንደተባለው፣ እንደአሁኑ ዘመን ህትመቱ ስንተኛው እንደሆነ ስለማይጠቀስ፣ የፅሁፉ የመጀመሪያ የድርሰት ጊዜ አይታወቅም፤ ከዘመኑ ምእራብ ቀመስ ባለሙያዎች ደግሞ ድንጋይ ላይ የተተወ ማስረጃ ካልተገኘ የሚሉም አሉ።ፕሮፌሰሩ በገፅ 25 ውስጥ ሙሉ ሰነድ አላየሁም ቢሉም፣ አለመታየቱ ግን ከአፈ-ታሪክ የተወሰደ ነው ለሚለው መላምት ማስረጃ አይሆንም። በሀገራችን ውስጥ ያሉንን ቅርሶች ሳናይ በማመን እንደምናውቃቸው ሁሉ ታሪኩንም ለማወቅ አይን ማስረጃ አይሆንም፣ልብእንጂ።
አጼ አምደ ፅዮን (ጀግናው በመባል የሚታወቁት) ያስፃፉት ታሪክ፣ ከአፈታሪክ የተውጣጣ ባይሆንም፣ የተወሰኑ ከሌላ መገልበጡን ይቃወማሉ።በንግስና ጊዜያቸውም ካልተስማሙት መካከል የግብፅ ጳጳሳትና  መነኮሳት ግንባር ቀደም ሲሆኑ እነርሱም ቢሆኑ የፅሁፍ ታሪክ እንደነበር አልካዱም።መሪራስ አማን በመፅሃፈ አብሪሂት ውስጥ አይነታቸውን፣ ርእሶቻቸውን፣ ብዛታቸውንና የታሪክ ሰነዶቹን ከየት እንዳመጡ ጭምር ይጠቅሳሉ። እርሳቸውም በተጉለት በመሪራስ ተድላ አለም ጥሪ እና መሪነት 12 ቅጂዎች እንደተባዙ መስክረዋል።
ያም ሆነ ይህ፣ እኔም ባለፉት አመታት በተለያዩ የሀገራችን ክፍሎች እየተዘዋወርኩ በአቅሜ የተወሰኑትን ለማረጋገጥ ችያለሁ።ከእነዚህም መካከል የፕሮፌሰር ፍቅሬአዲሱ መጽሃፍ ከሚያጠነጥንባቸው ታሪኮች አንዱ የሆነው የቀዳማዊ ምኒልክ ታሪክ ነው።የንግስተ ነገስት ሳባ (ኢትያ) ማክዳና የንጉስ ሰለሞን ልጅ የሆነው ምኒልክ፣ ሀገራችን ተመልሶ ያስገነባው የመጀመሪያዋን ቤተመቅደስ፣ አሁንም ቤተክርስቲያን የሆነችውን ለመመልከት በቅቻለሁ።
ተድባበ ፅዮን ትባል የነበረችው ይህች የአብያተ ክርስቲያናት ፈርጥ፤ በእድሜ ብዛት 9 ጊዜ ከመታደስ ውጪ እንዳለች ተድባበ ማርያም ተብላ ትገኛለች።የተተከለችበት ቦታ በኦሪት ዘመን የህብስትና ወይን መስዋዕት ይቀርብበት የነበረ ነው።ቀዳማዊ ምኒልክ በጊዜው የተከተሉትን 12 ሺ ገደማ የበኩር ልጅ አይሁዳውያንን ይዞ፣ ከካህኑ አዛርያስ ጋር እንደገቡ ሰፍረውበታል።በመላው የኢትዮጵያ ግዛት ለ12 ተከፍለው በነዋሪው ዘንድ ርስት ተሰጥቷቸው፣ በጋብቻ ከመዋለዳቸው በፊት የሰፈሩበት ይህ አካባቢ፤ አሁንም ድረስ እየሩሳሌም፣ እስራኤል ባሉ የቦታ ስያሜዎች (ገሊላን በመሳሰሉ) እየተጠሩ የሚገኙ ምሳሌያዊ ቦታዎችንና አስራ-ሁለቱንም መግቢዎችን ይዞ ይታያል።ይህም ታሪክ ተተንትኖ፣ የቦታው ባህልና ቱሪዝም በሚያወጣው በራሪ ፅሁፍ ላይ ተዘርዝሮ ይነበባል።
የአክሱም ፅዮንን ጥላተ ሙሴ ታሪክ፣ ታቦትዋ ባረፈችባቸው ቦታዎች የሚገኙ ነዋሪዎች የበለጠ እንደሚያውቁት፣ የግንደ መስቀሉንም እንዲሁ እኛ ኢትዮጵያውያን ታሪክንና ቅርስን በቤተሰብና በአካባቢ ይዘን የማቆየት ባህል ወርሰናል።በዚህም ምክንያት ሀገራዊ የታሪክ አለመግባባቶች ሲከሰቱ፣ የየአካባቢውን ታሪክ መዝግቦ የያዘው ማእከላዊው ወገን፣ ትክክለኛውን የመዳኘት ግዴታ አለበት።አሁን-አሁን የታሪኩ ያዦች ወገን መሆን የነበረብንም ጭምር ከሚጠራጠሩት ወገን እኩል ሆነን ለማረጋገጥ በመጣር ፋንታ ዳር እንቆማን። ዝም እንኳን ማለቱንም ትተን ለትችት እንቸኩላለን።
በአሁኑ ጊዜ ፕሮፌሰር ፍቅሬ ቶሎሳ፣ ተደብቆ የኖረውን ታሪክ ይፋ ለማውጣት ከሚደክሙ መካከል ግንባር ቀደሙን ቦታ ይይዛሉ።እንደ እርሳቸው፣ ይህን መፅሃፍ ለታሪክ ምሁራን መመራመሪያ ሳይሆን ለብዙሃናችንብለው ቀለል ባለ አጻጻፍ እንደወረደላቸው የፃፉት ነው።
“ታሪክ ለህዝብ እንጂ ለባለታሪኮች አይፃፍም”ይላሉ። ለሰው ልጅና ለእንስሳት ጨቅላዎች ወተት መሰረታዊ መብል እንደሆነ ሁሉ ይህ የእርሳቸው መፅሃፍ፣ የታሪክ ወተት ነው ለማለት ይቻላል። መፅሃፉ በማናቸውም ቦታ፣ በማንኛውም ሰው እንዲነበብ ሳይንዛዛ የቀረበ፣ ምሁራዊ ሀተታ ያልበዛበት እንደሆነ አስቀድመው ይነግሩናል።ታሪኩ ሃይማኖታዊ ስለመሆኑ፣ እውነታነቱን የእኛ ጊዜ አንባቢም ሆነ የወደፊት ታሪክ ፀሃፊ ሊቀይረው እንደማይገባና እንደማይችል፣ “የሆነው ሆነ ነው” በማለት ፅፈዋል።
እንደምሳሌ እንውሰድና፣ የቅዱስ ላሊበላን ወይም የአፄ ቴዎድሮስን ታሪክ ለህፃናት በአጭሩ እያዋዙ ቢነገራቸው ተረት ሊሆንላቸው ይችላል፤ ግን እውነተኝነቱን ነጋሪያቸው እስካልደበቃቸው ድረስ፣ አድገው ወደምግብ ሲሸጋገሩ በፍላጎት ይመገቡታል።
የመፅሃፉ ይዘት ከሌሎች የታሪክ መፅሃፎች የሚለየው ድብቅና ስውር የነበሩ ትላልቅ ወሳኝ ታሪኮችን በመያዙ ነው።እነዚህ የተደበቁ ሰነዶች ለእኛ ብቻ ሳይሆን ለአለም ጭምር አዲስ መሆናቸውን ፕሮፌሰሩ በመግቢያቸው ይነግሩናል።ይህም የሆነው ታሪኮቹ እንዲሰወሩ ሲያጠፏቸው የነበሩ እንዲሁም በተቃራኒው ወገን እንዲቆዩም ሲደብቋቸው የነበረ በመሆኑ ነው።ታሪኮቹን መደበቅና ማሳደድ በቀዳማዊ ምኒልክና በተወሰኑ ተቀናቃኝ ወገኖች ቢጀምርም ከ300 አመታት ግድም በላይ በአክሱማይ ዘመን ተመልሶ እየተፈራረቀ፣ እስከ ኢየሱስ ክርስቶስ መወለድ ድረስ ቆይቷል።
ይህን ታሪካዊ ወቅት፣ ማለትም የክርስትና መስፋፋት፣ የዘር የበላይነት በክህነት ስልጣን በኩል ቢያስቀርም፣ “ለሰውነት የበቃ ይበቃል” የሚለውን አስተምህሮ ግብፃውያኑ በማዛባት፣ ለፖለቲካዊ ጥቅም ሲሉ እኛ ብቻ ብለውት (ቃልን) በመቀየራቸው፣ በሌለንበትም በመወሰናቸው፣ የታሪክ አቅጣጫ ተቀይሯል። ግብፅን በእምነትና በሃይማኖት ታሪክ የበላይ አድርጐ ለማቅረብ የነበረው ጥረታቸው ከዚያ ቀደም የነበረውንም የኢትዮጵያ የፖለቲካ የበላይነት ለማስረሳትና ለመቀየር እስካሁን ጫና ለመፍጠር ይጥራሉ።ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ እኛ የመጣባቸውን ታሪኮች የራሳቸው ብቻ በማድረግ ጀመረ በሚባለው በዚህ ተግባራቸው፣ ይህን ታሪክ የያዙ የብራና ሰነዶች እንዲጠፉ በማድረግ ቀጥሎ ነበር።ይህም ጥቂት በማይባሉ ወደ ኢትዮጵያ በተላኩ የግብፅ የሃይማኖት አባቶች በግልፅም፣ በተዘዋዋሪም ተፈጽሟል።መንገዱ ቢለያይም ሰበብ እየፈለጉ ስያሜ እየሰጡ ሲያስተገብሩት መኖራቸው ተመዝግቧል።አሁን ግብፅውያንን ብቻ መሾሙን ብናቆምም፣ ትተውብን የሄዱትን የማይጠቅም አስተምህሮ መከተል ያልተውን ሰዎች አለን።እዚያም ሆነው የሚልኩብንን በመቀበል የተወሰንን ኢትዮጵያውያን እርስ በርሳችን በታሪክ እንዳንስማማና እንዳንረጋ አድርጎናል።
ታሪኩን ማንም ይደብቀው ወይም ያጥፋው እኛ ልጆቻችው፤ ከታሪክ ተጋሪዎቻችን ጋር በጋራምይሁንበተናጥልሁሉንምየታሪክጽሁፍአቅርበንበማየትመርምሮበመለየትወደትክክለኛውእንድንመጣ፣ይህየፕሮፌሰርፍቅሬ መጽሀፍመንገድጠቋሚካርታችንነው። ፕሮፌሰሩ ስለ ታሪክ ሲያነሱ ከማንነት ጋር እንደሚገናኝ ቃል በቃል፡- «ማንነታችን ጠንቅቀን ብናውቅ ኖሮ ዛሬ የገባንበት የማንነት ቀውስ ውስጥ አንገባምነበር፣»ብለውናል።ይህንንም በማስረጃ ሲያቀርቡ፣ በቅጣት የመጣውን የቋንቋ መለያየት መሠረት ያደረገ የጐሳ አስተሳሰብ፣ አሁን ወደ ሀገር-አቀፍ ደረጃ ተስፋፍቶ ወደ ብሄር መቀየሩን በገጽ 16 ላይ ያስረዳሉ።ይህም አሁን ከኢትዮጵያዊነታቸው ይልቅ ብሄራቸውን የሚያስቀድሙ ትክክል የሆኑ እንዲመስላቸው አድርጓል ይላሉ።ከልጅ አባት፣ ከአባት አያት እንደሚቀድም ሁሉ ከኢትዮጵያዊነታችን በኋላ የብሄር መገለጫችን ወይም የጐሳው አባት የሆኑት የልጆቹ ነገስታት ታሪክ እንደሚከተል ጠቅሰዋል።ይህንንም እውነታ ዘር እና ቋንቋ እንደሚለያይ፣ ዘር እንደማይቀያየር፣ እርስበርስ ግን እንደሚወራረሱ በግልጽ አፃፃፍ አሳይተዋል።
የኢትዮጵያ ህዝብና መንግስት ታሪክ ከአይሁዳውያኑ ታሪክ ጋር ስላለው ረጅም ግንኙነት የሚያስረዳው ይህ መጽሀፍ፤ ለአሁኖቹ እስራኤላውያን በተለይ አዲስ እና እንግዳ መሆኑ ግልጽ ነው።ይህ የሆነው ከኢትዮጵያዊው አማቱ ከሊቀካህኑ ዮቶርአብ የተማረው ታሪክና እውቀት በዝርዝር ለሙሴ ተከታዮች ባለመቅረቡ እንደሆነ ደራሲው በመግቢያቸው ያሳውቁናል።
ስለ ታሪኩ አመጣጥና ልዩነት፣ ስለ አቀባበሉም ይህን ካልን ስለ ይዘቱ በመጠኑ እናንሳ።ስለሁለቱ ህዝቦች ግንኙነት በመጽሀፍዋ ውስጥ ሲጀምር፣ ስለ ኢትዮጵያ አባት የኩሽ ወራሽ የመልከፀዲቅ የበኩር ልጅ ስለሆነው ኢትዮጵ እንዲሁምበዘመኑስለኖረውየሴምወራሽአብርሃምግንኙነትያብራራል።
በአብርሃም 5ኛ አባት ኤቦር እብራውያን የሚባሉት በልጅ-ልጅ-ልጁ ይሁዳ ደግሞ ይሁዳውያን የተባሉት ተለይተው መኖር በጀመሩበት በዚያ ጊዜም ታሪክ ያዥና በስርአት የተዋቀረ መንግስት እዚህ እንደነበረን በታሪክ የተመዘገበ ነው።የእነርሱ ታሪክ ያዥዎች ግን ከ500 አመታት በኋላ በሙሴ ዘመን እንደጀመሩ መጽሀፉ ይነግረናል።
አብርሃም ከገቢው 10-እጁን (አስራት) ለመልከፄዲቅ ማቅረቡ በመፅሀፍ ቅዱስ የተጠቀሰ ታሪክም፣ በታሪክ ሠነድነቱ ተቀባይነት አለው። ከሙሴ 500 አመታት ገደማ ዘግይቶ ስለተወለደው ዳዊትና ከተማው የተጠቀሰው ታሪክ መረጋገጡን በምሳሌነት በማቅረብ፣ የመፅሀፍ ቅዱስን ታሪካዊ ሠነድነትም በገጽ 18 ላይ አስታውቀዋል።   
ከአብርሃም ታሪክ ጀምሮ ከግብፅ በሙሴ ነፃ እስኪወጡ ድረስ የነበረ ግንኙነትን ጨምሮ በሙሴ ዘመንም ለ40 አመታት በሀገራችን የኖረበት የአማቱ የዮቶር አብ ታሪክና የውለታ ግንኙነትም በመጽሀፉ ውስጥ አንድ ምዕራፍ ተሠጥቶታል።
ከዚያ ጊዜ ወዲህ በአይሁዳውያኑእስራኤላውያንና በእኛ ዘንድ ያለውን የታሪክ አያያዝና አቀባበል የአሁን ዘመን እስራኤላውያንም ይለዩታል። ለዚህም አባባል የሀገሪቱ ምክር ቤት አፈጉባኤ ደብዳቤ ትርጉም ላይ «በኢትዮጵያውያን እይታ» የሚለው ስንኝ አስረጂ ይመስላል።
ይህን የታሪክ መለያየት በግልፅ የሚያስረዳው፣ የሁለቱ ህዝቦች ግንኙነት ስረ-መሰረቱ፣ የንጉስ ሰለሞንና የንግስተ-ነገስት ሳባ ግንኙነት እንደሆነ በሰፊው በእኛ ጭምር በመታመኑ ነው።ነገር ግን እውነታው ይህ እንዳልሆነ ፕሮፌሰሩ በመፅሀፋቸው ስለ ዳዊት እናት የዘር ሀረግ እንዲሁም ስለ ነብዩ በልዐም ታሪክና ሌሎችንም በመጥቀስ፣ ራሱን የቻለ ምዕራፍ በመመደብ፣ ከጅምሩም ግንኙነት እንደነበረን በቂ ማስረጃ አቅርበዋል።በቅርብ ምዕተ አመታት መለያየቱ እየበዛ አሁን ላለንበት መራራቅ እንዳደረሰ ቢታመንም የዛሬ 3ሺህ አመታት በፊት የጠነከረው ግንኙነት መመሳሰልን አስከትሎ ነበር።በኋላ ላይ የመለያየቱ ርዝመት ያስቀራቸው አለባበስን የመሳሰሉ ትውፊቶችም ተራርቀው ቢኖሩምስርአተ አምልኮቱ ተለያይቷል።
በሀገራችን ያለው አይሁዳውያንን “ኢየሱስ ክርስቶስን ያልተቀበሉ ዘሮች” አድርጐ የማየት አስተሳሰብ በአለም ህዝብ ዘንድም አለ።አይሁዳውያን ሆነው ክርስትናን የተቀበሉ በእስራኤል ጭምር ያሉ ቢሆንም እኛ ሀገር ያለነው የተዳቀልነው ጭምር በዘርና በሃይማኖት እየገለጹ፣ እየለያዩም፣ እያመሳሰሉም በማቅረብ እስከዛሬ ተገኝተናል።
በሀገራችን ታሪኩናባለታሪኮቹ የዘር ሀረግ የተወሳሰበ ቢሆንም ቀለል ባለ አቀራረብ በሀገራችን ቤተ እስራኤላውያን (የፈለሱ የሚባሉትን)የመጨረሻዎቹ መጪዎች እንጂ ጀማሪ እንዳልነበሩ በመጽሀፉ ተብራርቷል።  በሙሴ ልጆች እንደጀመረ የተፃፈው ታሪካዊ የዘር ግንኙነት፣ በነገስታቱ ውህደት ጸንቶ በህዝብ ቅልቅል የዛሬ 3ሺህ አመት በፊት የተስፋፋው ግንኙነት እስከ አሁን ለመኖሩ እኔም ሆንኩ እርስዎ የቁም/ተንቀሳቃሽ ማስረጃ እንደምንሆን እምነቴ ነው።ሁላችንም የአዳምና ሄዋን ልጆች፣ ከኖህ አባትነት የማንወጣ ስንሆን እኔም በኖህ ሁለቱ ልጆች ሴምና ካም በኩል ትውልዴን ለመቁጠር ችያለሁ። በሁለቱም የዘር ሀረጎች መካከል ሲገናኙ የ9 ትውልድ ልዩነት የነበረ ሲሆን አመዘጋገቡ ወንድ ቅድሚያውን ይይዛል። በዚህም ከአዳም በኩሽ ልጅ መስመር በሆነው መልከፀዲቅ በኩል እኔ 144ኛ ትውልድ ስሆን፣ ከሴም በአብርሃም በኩል በወረደው ደግሞ135ኛ እንደሆንኩ ለማረጋገጥ ችያለሁ።
መሪራስ አማን በላይም የዘር ሀረጋቸውን በተመሳሳይ በመፅሀፋቸው ውስጥ ጠቅሰውታል።
ስለ ግል ታሪክ ላብቃና የሀገራችንና የሁላችንም የሆነው ይህን ታሪክ በመሪራስ ባለ አደራዎች በሚገለፅበት ወቅት አቅም ባላቸው ምሁራን የበለጠ ሊብራራ እንደሚችል ፕሮፌሰር ፍቅሬ እምነታቸውን አስፍረዋል። እርሳቸው እንደሚሉት፤ “እኔ ባገኘሁት ትንሽዋ መረጃ ተመስርቼ በትንሽ አቅሜ የቻልኩትን አድርጊያለሁ፤ ታሪኩ ገና መጀመሩ ነው”፡፡ ይህም የታሪኩ ይፋ አውጪ የሆኑት የመሪራስ አማን በላይ ፍላጎት መሆኑን አስረድተዋል። እኛም በበኩላችን ማስረጃ ይሆናል ያልነውን ሄደን በመመርመር፣ ራሳችንንም በማሳተፍ መጣር እንደሚገባን ይናገራሉ። ይህንንም ለመግለፅ የታሪኩን መሰወር የሚመኙት ወገኖች ጨርሶ ለማጥፋት እንዳላረፉ በመጠቆም፣ እኛም ከተኛንበት እንንቀሳቀስ ብለዋል።እነዚህ የተደበቁ ታሪኮች ፈረንጆች ያለምንም ማስረጃ ከእኛው ባገኙት ተዘዋዋሪ ማስረጃ ጽፈው ሲያወጡ አለም ጭምር እንደማያንገራግር በግራሀም ሀንኩክ የታቦቱ ታሪክ (ፍለጋ) መጽሀፍ ጉዳዩን አስረድተውታል።በመሪራስ የተተረጎመው የኢየሱስ ክርስቶስን ታሪክ በአይኑ ያየውን የ3 አመት እማኝነት የፃፈውን ዜና ማርሄርን ለመቀበል ከግብፃውያን ተጽእኖ ራስን ማላቀቅ እንደሚገባ ተናግረዋል።
ፕሮፌሰሩ ስውር የነበሩ የኢትዮጰያውንና አይሁዳውያንን የጋራ ታሪኮችን በ14 ምዕራፎች ከፋፍለው ጽፈዋል።በመልከፀዲቅ እና አብርሃም ማንነትና ግነኙነት የጀመረው ይህ የተሠወረ የታሪክ ስነፅሁፍ ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ የግብፅ የልጅነት ቆይታ በኋላም የመርዌ እና የኢትዮጵያ ቆይታውን በማዋዛት ይቀጥላል።
ለረጅም ዘመናት ሲጠበቅ በነበረው በውልደቱ ወቅት ለኢየሱስ ክርስቶስ እና ለድንግል ማርያም ስጦታ ይዘው ስለሄዱት በ3ቱ ስር ስለነገሱት 12ቱ የኢትዮጵያ ግዛት ነገስታት፣ ማለትም ሰብአሰገል ተብለው ስለሚታወቁት ደጋግ ነገስታትም፣ ጽፈዋል።ከነገስታቱ እጅ መንሻ ማቅረብ 1,500 አመታት ገደማ በፊት በነብዩ ደሴት ጣና ላይ ከተነገረም ወዲህ በቀዳማዊ ምኒልክ 12ቱ የእስራኤል ልጆች ወራሾች ከነባር ሠፋሪዎች ጋር ተጋብተው፣ ተወላጆቻቸው ነገስታት ከ1ሺህ አመት በኋላ ሄደው፣ እንደ ትንቢቱ እጆቻቸውን ወደ ፈጣሪ በመዘርጋት ስጦታውን ማቅረባቸው በመጽሀፉ የተብራራ አንዱ የተደበቀ ስውር ታሪክ ነው።
የመጽሀፉ ምዕራፎች እንደጊዜያቸው ሳይሆን እንደ ጉዳዩ ርዕሱ ከሚኖረው ፋይዳ አኳያየታሪኮቹ መሠረትና ማረፊያቸው ስለሆነው ኢየሱስ ክርስቶስ ታሪክ በመተንተን ይቀጥላል።
ስለ ንግስተ ነገስታት ሳባና ቀዳማዊ ምኒልክ በአንድ ምዕራፍ ከሠፊው ታሪካቸው እየመረጡ ጽፈዋል።ስለ ሁለቱ ህዝቦች የቀድሞ የስልጣን ግንኙነትና ስለክርስትና እራሱን በቻለ መልኩ በማነፃፀር ለግንዛቤ አስፍረዋል።ስለ ዛጉዌ ክርስቲያናዊ ስርወ መንግስትና ስለ አይሁዳዊያኑ ግንኙነት መጠንከር በቀጣይ ምዕራፍ እንዲሁም በመጨረሻው የነብዩ ኤርምያስንና የኢትዮጵያዊውን አቤሜሌክ ወዳጅነት ዋቢ እያጣቀሱ አብራርተዋል።
ለአፍሪካ ስያሜ መነሻ የሆነው የአፋር ጐሳ ታሪክ በሴም ተወላጅ በዮቅጣን ልጅ ኦፌር ምድር ከመከፈሏ በፊት መጥተው ከነወንድሞቹ በተቀላቀሉ የተገኘ ስያሜ ነው።አፋሮች ስለነበራቸው ጥንታዊ የአለም ገናናነትበተርሴስ (አሁንአሰብአካባቢቀይባህርውስጥየሠመጠችየወደብከተማነች)በመጠቀም…ከእስራኤልጋርበመርከብስለነበረውግንኙነታቸውተጠቅሶአል።
በምድራቸውም ከድንጋይ በሚሰራ አቻ በሌለው መርከብ፣ የኦሮሞ ጐሳ አባላት የሆኑ የባህር ኃይሎች በማሳፈር፣ በንጉስ መጋል መሪነት እስከ ፖርትጋልና ስፔን ተዘምቶ፣ አገር እንደቀና ፕሮፊሰሩ በአጭሩ ቀንጭበው ጽፈውታል።
በመጨረሻ ልዕለሰብ ያሉትን ጉልበተኛና ኃያል ሰው ስለነበረው የሰው ልጆች ብቻ ሳይሆን የአራዊት ሁሉ ገዢ፣ የአለም ንጉስ ስለነበረው የእስያ አሰያሚ እስያኤል ወይም አፄ አስደማሚ ታሪክ ከብዙው በጥቂቱ ያስነብቡዋችኋል።ዱር ኖሮ ለመንገስ ሲመጣ የሚገጥመው አጥንቶ ከአናብስት ጉረኖ ገብቶ በቡጢ ስለመዘረሩ የተፃፈለት ይህ የጥበብ ሰው፤ እስከ ቻይና ድረስ የወርቅ ጋሻ በታጠቁ የሚሊዮኖች ሠራዊት አዝምቶ እየመራ አስገብሮ፣ የህግ ስርአትንና አነጋገስን ደንግጐ የተመለሰ የአለማችን ድንቅ ተአምረኛ ንጉስ ነው።10ኛ የልጅ-ልጁ ከሆነችው ንግስተ ነገስታት ሳባ ጋር ስለነበራቸው ግንኙነት የተፃፈ ሲሆን፣ እድሜ ጠግቦ በበቃኝ በፍላጐቱ በእርሷ ስለመገደሉ ቀለል ባለ አቀራረብ ደራሲው አቅርበውታል።እንድታነቡበትና የራሳችሁን ታሪክ እንድትጨምሩበትም በመጋበዝታሪኩንለብዙሃንጆሮናአይንፈጣሪእንዲያበቃውእመኛለሁ።                                                                               

Read 4155 times