Monday, 13 November 2017 10:19

“ሰውና ሰውነት” የግጥም መፅሐፍ ይመረቃል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)

  የገጣሚ ምናሴ ጌታሁን “ሰውና ሰውነት” የግጥም ስብስብ መፅሐፍ ዛሬ ከቀኑ 9፡00 ጀምሮ በራስ ሆቴል አዳራሽ ይመረቃል፡፡ ደራሲና ሀያሲ አስፋው ዳምጤ መፅሀፉን በክብር እንግድነት  ይመርቁታል ተብሎ እንደሚጠበቅ የምርቃቱ አዘጋጅና አስተባባሪ ጋዜጠኛ ጌታቸው አለሙ ለአዲስ አድማስ ገልጿል፡፡  
ደራሲ ጌታቸው በለጠና ደራሲና ገጣሚ ይታገሱ ጌትነት በመፅሀፉ ዙሪያ  ዳሰሳ የሚያቀርቡ ሲሆን ገጣሚያን ኢየሩሳሌም ነጋ፣ ንዋይ ከፍያለው፣ መስፍን ከፍአለ፣ አስቴር አስቻለውና ነቢያት አብደላ የግጥም ስራዎቻቸውን፣ ገጣሚ መዝገበ ቃል አየለ ቅኔ፣ እንደሚያቀርብና ወግና መነባንብ የዝግጅቱ አካል እንደሚሆን ታውቋል፡፡ በተለያዩ ርዕሠ ጉዳዮች ላይ የሚያጠነጥኑ ከ60 በላይ ግጥሞችን ያካተተው መፅሀፉ፤ በ72 ገፆች ተቀንብቦ፣ በ70 ብር ለገበያ ቀርቧል፡፡

Read 462 times