Monday, 13 November 2017 10:22

“አብዮት እንደበረከት” የስዕል ትርኢት ዛሬ ይከፈታል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)

 የገጣሚና ሰዓሊ ቸርነት ወ/ገብርኤል አዳዲስ ስራዎች ለእይታ የሚቀርቡበት “አብዮት እንደበረከት” የተሰኘ የስዕል ትርኢት በኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ፣ በብላቴን ጌታ ህሩይ ወልደስላሴ ስም በተቋቋመው የስነ-ጥበባት ማዕከል ዛሬ ከቀኑ 9፡00 ጀምሮ ይከፈታል፡፡
ሳይንስ አካዳሚው ለመጀመሪያ ጊዜ በሚያካሄደው የስዕል ትርኢት ላይ የገጣሚና ሰዓሊ ቸርነት ወ/ገብርኤል  27 ሥራዎች ለተመልካች የሚቀርቡ ሲሆኑ ሰዓሊው በአካዳሚ በተሰጠው ዕድል ላለፉት አራት ወራት እዚያው እየኖረ ቀንና ሌሊት የሳላቸው አዳዲስ ስራዎች በአውደ ርዕዩ ይታያሉ ተብሏል፡፡
 የስዕል ትርኢቱ ለሁለት ወራት ያህል ለእይታ ክፍት ሆኖ እንደሚቆይም ታውቋል፡፡ የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ ከ2009 ዓ.ም ጀምሮ በብላቴን ጌታ ህሩይ ወልደስላሴ ስም የስነ-ጥበባት ማዕከል ከፍቶ፣ ከሌሎች ሳይንሳዊ ክንዋኔዎች ጎን ለጎን በስነ-ጥበቡ እየተንቀሳቀሰ እንደሚገኝ ለማወቅ ተችሏል፡፡

Read 743 times