Monday, 13 November 2017 10:28

የተባባሪ ፕ/ር ተስፋዬ ገሰሰ “የመጨረሽታ መጀመርታ” መፅሀፍ ለንባብ በቃ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(2 votes)

   የቴአትር ምሁር፣ ደራሲና ተርጓሚ ተባባሪ ፕሮፌሰር ተስፋዬ ገሰሰ “የመጨረሽታ መጀመርታ”- የተሰኘ ታሪክና ህይወት ቀመስ ሽሙጥ ልቦለድ መፅሀፍ ለንባብ በቃ፡፡ ደራሲ ስብሀት ገ/እግዚአብሄርንና ደራሲና ጋዜጠኛ በዓሉ ግርማን ማዕከል አድርጎ የተፃፈው ልቦለድ፤ የሁለቱን ሰዎች ህይወትና ታሪክ በቀልድና ጨዋታ አዋዝቶ የሚያስቃኝ ነው ተብሏል፡፡ በ114 ገፆች የተቀነበበው መፅሀፉ፤ በ50 ብር ለገበያ ቀርቧል፡፡
ተባባሪ ፕሮፌሰር ተስፋዬ ገሰሰ ከዚህ ቀደም የኡመር ኻያምን ሩቢያቶች የግጥም መድበል ጨምሮ በርካታ ድርሰቶችን፣ ትርጉሞችንና የተውኔት ፅሁፎችን ለንባብ ማብቃታቸው ይታወሳል፡፡

Read 3183 times