Monday, 13 November 2017 10:20

“76ኛው ግጥም በጃዝ” ረቡዕ ይካሄዳል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(1 Vote)

76ኛው ግጥም በጃዝ የኪነ-ጥበብ ምሽት የፊታችን ረቡዕ ከቀኑ 11፡30 ጀምሮ በራስ ሆቴል ይካሄዳል፡፡ ገጣሚና ተርጓሚ ነቢይ መኮንን፣ አርቲስት ፍቃዱ ተ/ማሪያም፣ አርቲስት ጌትነት እንየውና መንግስቱ ዘገዬ የግጥም ስራዎቻቸውን የሚያቀርቡ ሲሆን በዲያቆን ዳንኤል ክብረት ዲስኩር እንደሚቀርብ ገጣሚ ምስራቅ ተረፈ ገልፃለች፡፡
በፕሮግራሙ ላይ በዶ/ር በድሉ ዋቅጅራ የተደረሰ “ደብተራው” የተሰኘ አጭር ተውኔት በአርቲስት ሽመልስ አበራና በእታፈራሁ መብራቱ ትወና ለታዳሚ የሚቀርብ ሲሆን ገጣሚና ተርጓሚ ጋዜጠኛ ነቢይ መኮንን ሰሞኑን ከዚህ ዓለም በሞት ስለተለየው ገጣሚና የፍልስፍና ሊቅ ሰለሞን ደሬሳ ይናገራል ተብሏል።

Read 634 times