በጥቅሉ ወደ 20 ሺ ብር ገደማ ይሆናል። የጤና፣ የትራንስፖርት እና የመኖሪያ ቤት አገልግሎቶችን ጨምሮ፤ የበረራ አስተናጋጆቹ የተለያዩ ጥቅማ ጥቅሞች ከአየር መንገዱ እንደሚያገኙም ሃላፊው ተናግረዋል።አየር መንገዱን በመወከል የቅጥር ውድድሩን ሲያከናውኑ የነበሩት የካቤ ዋና ስራአስኪያጅ አቶ ሁሴን ሰኢድ በበኩላቸው፤ የበረራ አስተናጋጆቹ በብቃት ስራቸውን እንደሚወጡ እምነታቸው መሆኑን ጠቅሰው፤ የሁለቱም አገራት አምባሳደሮች ናችሁ ብለዋል። አየር መንገዱ ስድሳ የበረራ አስተናጋጆችን ከኢትዮጵያ እንደሚቀጥር ካሁን ቀደም ተዝግቦ እንደነበር ይታወሳል።አሁን የተካሄደው የቅጥር ውድድር የመጀመሪያ ዙር እንደሆነና በሁለቱ አገራት ግንኙነት አዲስ መንገድ የሚከፍት መሆኑን የተናገሩት አቶ ሁሴን ሰኢድ፤ ይህን ግንኙነት የሚያስፋፉ ተጨማሪ ዙሮች ይቀጥላሉ ብለዋል።በዚሁ ውድድር አንድ ሺ ሴቶች የተሳተፉ ሲሆን፤ አሁን ለቅጥር ፎርም የሞሉት 43 ሴቶች የሳዑዲ ጉዟቸው መቼ እንደሚሆን ከሚቀጥለው ሳምንት ጀምሮ ይነገራችኋል ተብለዋል።