Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 14 April 2012 12:39

ራስል ብራንድ ፍቺ የስነ ልቦና ቀውስ አድርሶበታል የ20ሚ. ዶላር ኪሳራ ገጥሞታል

Written by 
Rate this item
(0 votes)

እንግሊዛዊው የፊልም ተዋናይ ራስል  ብራንድ ከ27 ዓመቷ አሜሪካዊ ድምፃዊት ኬቲ ፔሪ ጋር የመሰረተውን ትዳር ካፈረሰ በኋላ በመጥፎ ተግባሮቹ የሚዲያ ትኩረት ስቧል፡፡ ከፍቺው ጋር በተገናኘ ከ20 ሚሊዮን ዶላር በላይ እንደከሰረ ተገለፀ፡፡ ፍቺውና ኪሳራው የሥነ ልቦና መቃወስ ሳያደርስበት እንዳልቀረም ተገምቷል፡፡ የ36 ዓመቱ እንግሊዛዊ ራስል ብራንድ በቢቢሲ ሬድዮ 2፤ በእንግሊዝ የሱስ ችግሮች ላይ የሚያጠነጥን ቶክ ሾው በመስራት ላይ ሲሆን በሬድዮ በሚያቀርባቸው አንዳንድ አስተያየቶች አወዛጋቢ እየሆነ መምጣቱን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

ራስል ብራንድ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በተወነባቸው ሰባት ታዋቂ ፊልሞች በዓለም ዙርያ እስከ 1.2 ቢሊዬን ዶላር ገቢ በማስገኘት ከእንግሊዝ ተዋናዮች በላቀ ደረጃ ላይ የሚገኝ ባለሙያ ነው፡፡ ራስል ብራንድ ፍቺ ከፈፀመ በኋላ የሚያሳያቸው ባህሪያት በስነልቦና ችግር ውስጥ እንደሚገኝ አመላካች ነው ያለው የቲኤም ዜድ ዘገባ፤ ሰሞኑን ሞባይሉን እንክትክት አድርጎ ሲሰባብር መታየቱንና የዶላር ኖት ሲያቃጥል ተገኝቶ ለፖሊስ ቃሉን እንደሰጠ ጠቁሟል፡፡

 

 

 

Read 1937 times Last modified on Saturday, 14 April 2012 12:45