Saturday, 18 November 2017 13:40

ሮሚያ ህብረት ባንክ ከ “IBM” ኩባንያ ጋር እየሰራ ነው

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)

ቅርንጫፎቹን በ25 በመቶ ለማሳደግ አቅዷል
               
   ከተቋቋመ 12 ዓመታትን ያስቆጠረው የኦሮሚያ ህብረት ባንክ አሰራሩን ለማዘመንና የዳታ ቤዝ መሰረተ ልማቱን ለማጠናከር፣ “IBM” ከተሰኘ ቴክኖሎጂ አቅራቢ ኩባንያ ጋር አብሮ ለመስራት ባለፈው ረቡዕ በኒዮርክ ተፈራረመ፡፡ ባንኩ ካሉት ቅርንጫፎች 25 በመቶ ያህል ተጨማሪ ቅርንጫፎችን ለመክፈት እቅድ መያዙም ታውቋል።
ከ2.4 ሚሊዮን በላይ ደንበኞች ያሉት ባንኩ፤ ቴክኖሎጂውን ከመጠቀሙ በፊት በሚሰጣቸው አገልግሎቶች ላይ የሲስተም መቆራረጥና የስራ መጓተት ሲያጋጥመው እንደነበርና ከቴክኖሎጂ አቅራቢው ጋር መስራት ከጀመረ በኋላ በአሰራሩ ላይ ከፍተኛ ለውጥና መሻሻል መታየቱን የባንኩ ሀላፊዎች ጠቁመዋል፡፡ ቀደም ሲል የባንኩ ሰራተኞች አንድ የንግድ ልውውጥ ላይ ከ3 ሰዓት በላይ ይፈጁ እንደነበር የገለፁት ሃላፊዎች፣ ባንኩ ቴክኖሎጂውን መጠቀም ከጀመረ በኋላ የንግድ ልውውጥ ስራው ከአንድ ሰዓት ባነሰ  ጊዜ ውስጥ እንደሚከወን ገልፀዋል፡፡
“IBM” ኩባንያው በቀጣይ ለባንኩ ወሳኝ የሆኑ ቁልፍ ቴክኖሎጂዎችን ጨምሮ በማቅረብ የባንኩን ችግር ሙሉ ለሙሉ እንደሚቀርፍ ገልጿል፡፡ “IBM” በ170 የዓለም አገራት ተመሳሳይ ቴክኖሎጂ በማቅረብ ተቀባይነት ያለው ዓለም አቀፍ ድርጅት መሆኑም ታውቋል፡፡

Read 2290 times