Saturday, 25 November 2017 09:19

መንግስት ተጨማሪ 70 ሺህ ቶን ስንዴ ለመግዛት ዓለማቀፍ ጨረታ አወጣ

Written by  አለማየሁ አንበሴ
Rate this item
(4 votes)

   የኢትዮጵያ መንግስት ተጨማሪ 70ሺህ ቶን ስንዴ ለመግዛት አለማቀፍ ጨረታ ማውጣቱ የተገለፀ ሲሆን ከጥቂት ቀናት በፊት 400 ሺህ ቶን ስንዴ በዓለማቀፍ ጨረታ መግዛቱ ይታወቃል፡፡ የአሁኑ ጨረታ የወጣው የስንዴ ግዥው በቂ ባለመሆኑ ነው ተብሏል፡፡
የዓለም ባንክ የመረጃ ምንጮች እንደጠቆሙት፤ የዘንድሮ የስንዴ ግዥ ካለፈው አመት ጋር ሲነፃፀር ከፍተኛ ሲሆን ለግዥው የሚውለው ገንዘብም ከአለም ባንክ አለማቀፍ የልማት ማህበርና ከሌሎች ለጋሾች በእርዳታ የተገኘ ነው፡፡
ሀገሪቱ በየዓመቱ ከግማሽ ሚሊዮን ቶን ያላነሰ ዓለማቀፍ የስንዴ ግዥ እንደምትፈፅም  የሚጠቁሙት መረጃዎቹ፤ ይህም ኢትዮጵያ እስካሁን በሀገር ውስጥ ምርት የህዝቧን የቀለብ ፍጆታ መሸፈን እንደተሳናት ያመለክታል ተብሏል፡፡ በግዥ ወደ ሀገር ውስጥ የሚገባው ስንዴ፤ የሀገር ውስጥ ምርት ጉድለትን ለመሸፈን እንደሚውል ይታወቃል፡፡

Read 3319 times