Saturday, 25 November 2017 10:36

“ብዥታ” የግጥም መድበል እየተሸጠ ነው

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(1 Vote)

    እውቁ ደራሲና ገጣሚ አስማማው ኃይሉ (አያሻረው) በሕይወት ሳለ ለህትመት አሰናድቶት የነበረውና “ብዥታ” የተሰኘ የግጥም ስብስብ መፅሐፍ በቤተሰቦቹ አማካኝነት ታትሞ  ሰሞኑን ለንባብ በቃ፡፡ በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ የሚያጠነጥኑ ግጥሞችን ያካተተው ባለ 104 ገፆች  መፅሀፉ፤ በ40 ብርና በ10 ዶላር ለገበያ ቀርቧል፡፡ በሌላ በኩል ደራሲው በህይወት ሳለ ያሳተመውና ተወዳጅነትን ያገኘለት “ከደንቢያ-ጎንደር እስከ ዋሽንግተን ዲሲ” የተሰኘው ቁጥር 1 ታሪካዊ ልቦለድ መፅሐፉ ለሁለተኛ ጊዜ ታትሟል፡፡ በ210 ገፆች የተቀነበበው መፅሃፉ በ60 ብ ከ70 ሳንቲም እየተሸጠ ነው፡፡

Read 1691 times