Print this page
Saturday, 25 November 2017 10:37

“የተራማጆቹ መጨረሻ” ለንባብ በቃ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(1 Vote)

በደራሲ የእዮብዘር ዘውዴ የተዘጋጀውና ከ1930 እስከ 1970ዎቹ በዘመናዊት ኢትዮጵያ የተደረጉ እንቅስቃሴዎችን በስፋት የሚያስቃኘው “የተራማጆቹ መጨረሻ” የተሰኘ መፅሀፍ ለንባብ በቃ፡፡ በአምስት ዋና ዋና ክፍሎችና በበርካታ ንዑስ ክፍሎች የተከፋፈለው መፅሀፉ፣ በዘመናዊ ኢትዮጵያ የተደረጉ የፖለቲካዊ ለውጥ እንቅስቃሴዎችን ያስቃኛል፡፡ በብዙ ድካም ስለተገነባው ክብር ዘበኛ፣ ስለ ታህሳሱ ግርግር፣ ስለ መንግስቱ ነዋይ ኩዴታና ሌሎችም ታሪካዊ ክስተቶች ይዳስሳል፡፡ በ386 ገፅ የተመጠነው መፅሀፉ፤ በ152 ብር ለገበያ ቀርቧል፡፡

Read 1599 times