Saturday, 14 April 2012 12:54

“ስልክሽን ልያዘው” እና “ማጎርሚሳቢብ” ለንባብ በቁ

Written by  መልካሙ ተክሌ (melkamutekele@gmail.com)
Rate this item
(0 votes)

በገነነ ግርማ የተዘጋጁ ግጥሞች እና አጭር ልቦለዶች የተካተቱበት መፅሐፍ ለንባብ በቃ፡፡ በፊት ለፊት በኩል “ፊትለፊት ስንኞች” በሚል ርእስ 58 ግጥሞች በጀርባ በኩል “ስልክሽን ልያዘው? እና ሌሎች” ስድስት ታሪኮች የተካተቱበት መፅሐፍ ዋጋ 29 ብር ነው፡፡ በሌላም በኩል “ማጎርሚሳቢብ” ልቦለድ መፅሐፍ ከትናንት ወዲያ ከማተሚያ ቤት በመውጣት ለንባብ በቃ፡፡ በአሰግድ መኮንን የተፃፈው ባለ 304 ገፅ መጽሐፍ ለሀገር ውስጥ ገበያ 65.80 ብር ለውጭ ሀገራት 35 የአሜሪካ ዶላር ይሸጣል፡፡ ደራሲው ካሁን በፊት “ኮብላይ”፣ “ጥብቅ ምስጢር” እና “ነፀብራቅ” በሚሉ መፃሕፍቶቻቸው ይታወቃሉ፡፡

 

 

Read 1808 times Last modified on Saturday, 14 April 2012 13:03