Sunday, 03 December 2017 00:00

በቀን 969 በረራዎችን ያስተናገደው የህንዱ አውሮፕላን ጣቢያ ክብረ ወሰን ያዘ

Written by 
Rate this item
(0 votes)

 ከአገሪቱ ዜጎች 75 በመቶው በአውሮፕላን ተጉዘው አያውቁም

    ባለፈው ሳምንት አርብ ብቻ በድምሩ 969 በረራዎችን ያስተናገደው የህንዱ ሙምባይ አለማቀፍ የአውሮፕላን ማረፊያ ጣቢያ በአንድ ቀን ውስጥ በርካታ በረራዎችን በማስተናገድ ክብረ ወሰን መያዙን ፎርቹን ዘግቧል፡፡
ሁለት የማኮብኮቢያ መስመሮች ቢኖሩትም በአንዴ በረራ ለማካሄድ አመቺ ባለመሆናቸው በአንዱ ብቻ የሚጠቀመው የሙምባይ አለማቀፍ የአውሮፕላን ማረፊያ ጣቢያ፣ በአንድ መስመር በአንድ ቀን ይህን ያህል በረራ በማስተናገድ ታሪክ መስራቱን የጠቆመው ዘገባው፤ ከዚህ በፊት በአንድ ቀን እስከ 900 የሚደርሱ በረራዎችን ያስተናግድ እንደነበር አስታውሷል፡፡ የሙምባይ አለማቀፍ የአውሮፕላን ማረፊያ ጣቢያ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎችን ጠቅሶ ዘገባው እንዳለው፣ በቀጣይም ዕለታዊ የበረራ መስተንግዶውን 1 ሺህ በማድረስ ክብረ ወሰኑን ለማሻሻል ዝግጅት እየተደረገ ይገኛል።
የህንድ አየር መንገዶች ባለፈው አመት ብቻ 100 ሺህ ያህል የአገር ውስጥ መንገደኞችን ማመላለሳቸውን የጠቆመው ዘገባው፤ ይህን ቁጥር በመጪው አመት 437 ለማድረስ እየተሰራ እንደሚገኝም አመልክቷል፡፡
ስፓይስጄት የተባለውን የአገሪቱ አየር መንገድ ጠቅሶ ዘገባው እንዳለው፣ ከአጠቃላዩ የአገሪቱ ህዝብ 75 በመቶ የሚሆኑት ወይም 1.3 ቢሊዮን ህንዳውያን፣ በህይወት ዘመን ቆይታቸው አንድም ጊዜ በአውሮፕላን ተሳፍረው አያውቁም፡፡

Read 1455 times