Saturday, 02 December 2017 08:56

“የኢትዮጵያና የጣሊያን ሁለተኛው ጦርነት ታሪክ” ላይ ውይይት ይደረጋል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)

 የደራሲ ጥላሁን ጣሰው “የኢትዮጵያና የጣሊያን ሁለተኛው ጦርነት ታሪክ” መፅሐፍ የፊታችን ማክሰኞ በብሔራዊ ቴአትር አዳራሽ ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ጀምሮ ውይይት ይደረግበታል፡፡
በቡክላይት መፃህፍት መደብር አዘጋጅነት በሚደረገው ውይይት ላይ የመነሻ ሃሳብ የሚያቀርበው የታሪክ፣ የሥነ-ዜጋና የህግ ምሁሩ ወጣት ደጀኔ ወልደጨርቆስ እንደሆነ ተጠቁሟል፡፡ የመፅሃፉን ጥበባዊ ትርክትና አቀራረብ በተመለከተ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የቴአትር ጥበባት ረዳት ፕሮፌሰር ነብዩ ባዬ እንዲሁም የሥነ-መለኮትና ሊደርሺፕ ምሁር  ዶ/ር ዘካሪያስ አምደብርሃን ደግሞ የአርበኞችን የአመራርና የማስተባበር ችሎታ ከሊደርሺፕ አንፃር የሚዳስስ ጥናት ያቀርባሉ ተብሏል፡፡ በተጨማሪም “የሽንቁጥ ልጆች” መፅሐፍ ደራሲና የጥንታዊት ኢትዮጵያ አርበኞች ምክትል ፕሬዚዳንት አምባሳደር ዓለማየሁ ሽንቁጥና በመሳጭ ዲስኩሮቻቸው የሚታወቁት መጋቢ ሀዲስ እሸቱ ዓለማየሁ ዲስኩር እንደሚያቀርቡ የዝግጅቱ አስተባባሪ አቶ በፍቅሩ ዳኛቸው ገልፀዋል፡፡
“የኢትዮጵያና የጣሊያን ሁለተኛው ጦርነት ታሪክ” የጦርነቱን አጠቃላይ ሂደትና ገፅታ በጥናት አስደግፎ የሚተነትን መፅሐፍ ሲሆን በ223 ገፆች ተቀንብቦ የተሰናዳ ነው፡፡

Read 884 times