Saturday, 02 December 2017 08:53

“አርት ኦፍ ኢትዮጵያ” 10ኛ ዙር ኤግዚቢሽን በሸራተን ይከፈታል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(2 votes)

አንጋፋና ወጣት ሰዓሊያን የሚሳተፉበት “አርት ኦፍ ኢትዮጵያ” 10ኛ ዙር ኤግዚቢሽን የፊታችን ረቡዕ በሸራተን አዲስ ሆቴል ላሊበላ አዳራሽ ከምሽቱ 12፡00 ሰዓት ጀምሮ ይከፈታል፡፡ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር ይከፍቱታል በተባለው በዚህ ዓመታዊ የስዕል አውደርዕይ ላይ ከ400 በላይ የሆኑ የ60 ሰዓሊያን ስራዎች ለእይታ ይቀርባሉ ተብሏል፡፡ ከህዳር 27 ቀን 2010 ዓ.ም  ጀምሮ ለህዝብ እይታ ክፍት የሚሆነው ኤግዚቢሽኑ፤ እስከ ታህሳስ 1 ቀን 2010 ዓ.ም እንደሚቆይም ሸራተን አዲስ የላከው መግለጫ ያመለክታል፡፡
በተያያዘም “አርት ኦፍ ኢትዮጵያ” ዓመታዊ የስዕል አውደርዕይ በሸራተን አዲስ የተጀመረበት 10ኛ ዓመት በዓልም እንደሚከበር ተገልጿል፡፡

Read 1250 times