Monday, 04 December 2017 00:00

ብሔራዊ የመፅሐፍት አውደርዕይ ማክሰኞ ይከፈታል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)

 “ከአንድ አስተዋይ ሰው ጀርባ መፃህፍት አሉ”

    ከ11 በላይ የመፅሐፍት አከፋፋዮች ያዘጋጁትና የሚሳተፉበት ብሔራዊ የመፅሐፍት አውደ ርዕይ በብሔራዊ ቴአትር ጋለሪ አዳራሽ፣የፊታችን ማክሰኞ ረፋድ ላይ እንደሚከፈት ተገለጸ፡፡
 “ከአንድ አስተዋይ ሰው ጀርባ መጻህፍት አሉ” በሚል መሪ ቃል የሚካሄደው ይኸው አውደ ርዕይ፤ እስከ ታህሳስ 2 ቀን 2010 ዓ.ም ለተከታታይ ስድስት ቀናት ለጎብኚዎች ክፍት ሆኖ እንደሚቆይ ታውቋል፡፡ አውደ ርዕዩ በተለይ ወጣቱ ከአልባሌ ቦታ ርቆ መፅሐፍት በማንበብ ጊዜውን እንዲያሳልፍ በአማራጭነት የቀረበ ነው ተብሏል፡፡ ቀጣይነት እንደሚኖረው በተነገረለት በዚህ አውደ ርዕይ ላይ ከአለማዊ እስከ መንፈሳዊ መጻህፍት ድረስ በስፋት እንደሚቀርቡ የገለፁት አዘጋጆቹ፤ ለተማሪዎችና ለመምህራን አጋዥ የሆኑትን ጨምሮ ከገበያ የጠፉና የማይገኙ መፃህፍት ከ20-50 በመቶ ቅናሽ ተደርጐባቸው ለሽያጭ እንደሚቀርቡም የአውደ ርዕዩ አስተባባሪ አቶ በፍቅሩ ዳኛቸው ገልፀዋል፡፡

Read 1590 times