Print this page
Sunday, 03 December 2017 00:00

የፈለቀ አበበ የአጫጭር ልብወለዶች ትርጉም ለንባብ በቃ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(1 Vote)

የዕውቁ ተዋናይ የአርቲስት ፈለቀ አበበ የአጫጭር ልብወለዶች ትርጉም ስብስብን ያካተተው “የከተማው ዘላን” የተሰኘ መፅሐፍ ሰሞኑን ለንባብ ቀረበ፡፡
አርቲስቱ ለረዥም ጊዜያት የተለያዩ መጣጥፎችና አንጋፋው የውጭ ደራሲያንን የአጭር ልብወለዶች እየተረጎመ ለአዲስ አድማስ አንባቢያን ሲያቀርብ መቆየቱ የሚታወስ ሲሆን፣ ቀደም ሲል በጋዜጣው ላይ ያስነበባቸውን 16 ያህል አጫጭር ልብወለዶች አሰባስቦ ለህትመት አብቅቷል፡፡ ከሥራዎቹም መካከል የቺኑዋ እቼቤ “ያገር ሰላም”፣ የማርክ ትዊይን “የሰዓሊው እረፍት”፣ የካህሊል ጂብራን “ትናንት እና ዛሬ”፣ የኤድጋር አለንፖ “ህያው ልብ” የሚሉት ይገኙበታል፡፡ ልብ ወለዶቹ፤ በደራስያኑ አጫጭር የህይወት ታሪክ ገለፃዎችና ምስሎችም የታጀቡ ናቸው፡፡ አሳታሚው ጃዕፋር መፃህፍት ሲሆን የታተመው በፋር ኢስት ትሬዲንግ ነው፡፡ የግጥም ምርቃቶቹን ጨምሮ በ176 ገፆች የተቀነበበው “የከተማው ዘላን፤ በ61 ብር ለአንባቢያን ቀርቧል፡፡
“ማርክ ትዌይን…ገና አፉ እንደፈታ ነበር ተረት ማውራት የጀመረው ይባላል፡፡ ከሰዓታት በኋላ ዕውቅ ወግ ጠራቂ ወጣው - ታላቅ ፀሀፊ ሆነ፡፡ በድርሰቶቹ፣ አንባቢያኑን በአስደናቂ ምናባዊ ጉዞ ማንሳፈፍን ተክኖበታል፡፡ አንባቢው ከታሪክ ነጋሪው ጋር የሚጋራው ዓለም ያገኛል፡፡ በቃ፣ ልክ አንድ የልጅነት አብሮ አደግ ጓደኛችንን አግኝተን የምናወጋ ያህል እንዲሰማን ያደርጋል፡፡…” ይላል-በገፅ 21 ላይ የቀረበው የማርክ ትዌይን አጭር የህይወት ታሪክ ገለፃ በከፊል ሲነበብ፡፡

Read 5177 times