Saturday, 09 December 2017 13:09

ግብፅ የህዳሴ ግድቡን ግንባታ ማስቆም እንደማይቻላት አስታወቀች

Written by  አለማየሁ አንበሴ
Rate this item
(23 votes)

 ለግብፃውያን የአባይ ውሃ የህልውና ጉዳይ ቢሆንም በወንዙ ላይ ኢትዮጵያ እየገነባች ያለውን የታላቁ ህዳሴ ግድብ ሀገራቸው ግብፅ ማስቆም እንደማይቻላት የሀገሪቱ የውሃ ሚኒስትር አስታወቁ።
የግብፅ የውሃ እና መስኖ ሚኒስትር ሞሃመድ አብደል አቲ፤ ሀገራቸው ግብፅ ግድቡን ለማስቆም እንደማይቻላት መረዳቷን፣ ነገር ግን በውሃው አጠቃቀም ላይ አሁንም አዳዲስ የመፍትሄ ሃሳቦችን በማቅረብ ከሱዳንና ከኢትዮጵያ ጋር እንደምትደራደር መግለፃቸውን አረብ ኒውስ ዘግቧል፡፡
ግብፅ የምታቀርበውን አዲስ አማራጭ ለጊዜው ለመግለፅ እቸገራለሁ ያሉት ሚኒስትሩ፤ግድቡ ግን 97 በመቶ የግብፅ ህዝብ ጥገኛ የሆነበትን የአባይ ወንዝ ፍሰት መጠን እንደማይቀንስ ማረጋገጥ እንፈልጋለን ብለዋል፡፡
የግብፅ የመስኖ እርሻ 80 በመቶ በአባይ ውሃ ላይ ጥገኛ መሆኑን የጠቆሙት ሚኒስትሩ፤ የሀገሪቱ ህዝብ ቁጥርም በ2050 እ.ኤ.አ ወደ 170 ሚሊዮን እንደሚደርስና የዚህን ህዝብ ህልውና ማረጋገጥ ደግሞ አሁን ያለው ትውልድ ኃላፊነት መሆኑን ተናግረዋል፡፡    

Read 11751 times