ሚዩዚክ ሜይዴይ ኢትዮጵያ፣ ከኢትዮጵስ ኮሌጅ ጋር በመተባበር፣ ነገ ከቀኑ 8፡00 ጀምሮ በገጣሚ በላይ በቀለ ወያ “ከሴተኛ አዳሪ የተኮረጀ ሳቅ” በተሰኘ የግጥም መድበል ላይ በብሄራዊ ቤተ መፃህፍትና ቤተ-መዛግብት ኤጀንሲ አዳራሽ ውይይት ያካሂዳል፡፡
ለውይይቱ የመነሻ ሀሳብ የሚያቀርቡት ገጣሚና ሀያሲ ደረጀ በላይነህ ሲሆኑ ፍላጎት ያለው በውይይቱ ላይ እንዲሳተፍ ሚዩዚክ ሜይዴይ ጋብዟል፡፡
Saturday, 09 December 2017 13:45
“ከሴተኛ አዳሪ የተኮረጀ ሳቅ” ላይ ነገ ውይይት ይካሄዳል
Written by ናፍቆት ዮሴፍ
Published in
ኪነ-ጥበባዊ ዜና