Saturday, 09 December 2017 13:48

“ምትሀት-ንድፍ” የፎቶግራፍ አውደ ርዕይ ተከፈተ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)


    በተለያዩ መድረኮች ግጥሞችን በማቅረብ የሚታወቀውና የፎቶግራፍ ባለሙያው በክሪ አህመዲን ከ35 በላይ የፎቶግራፍ ስራዎች ለእይታ የቀረቡበት “ምትሀት-ንድፍ” የተሰኘ የፎቶግራፍ አውደርዕይ ከትላንት በስቲያ ሀሙስ ከ11፡00 ጀምሮ በፈንዲቃ “ኢትዮ ከለር” የስዕል ጋለሪ ተከፈተ፡፡ የፎቶግራፍ አውደርዕዩ  በኢትዮጵያ የቡና አፈላል ስነ-ስርዓት ላይ የሚያጠነጥን ሲሆን ተሰቅለው ለእይታ ከሚበቁ ፎቶግራፎች በተጨማሪ በአሸዋና በተለያዩ ሸክላዎች ወለል ላይ የሚሰናዳ የጥበብ ትርኢትም ለተመልካች እንደሚቀርብ ታውቋል፡፡
በዓይነቱ ለየት ያለውና የቡና ዱቄትን በጥብጦ በመድፋት የሚመጣውን ቅርፅ ፎቶግራፍ አንስቶ የተለየ ውበት በማላበስ ለእይታ የሚያበቃው አውደ ርዕዩ፤ እስከ ታህሳስ 14 ቀን 2010 ዓ.ም ለእይታ ክፍት ሆኖ ይቆያል ተብሏል፡፡

Read 853 times