Print this page
Saturday, 09 December 2017 13:49

“አሻሮ መንጋ” የፖለቲካ መፅሐፍ ለንባብ በቃ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)

 “የኛ ፓርቲ ገና አልተወለደም” - ደራሲው

    በህዝብ አስተዳደር ትምህርት የሁለተኛ ዲግሪ ምሩቅ የሆኑትና የህዝብ ግንኙነት ባለሙያና ጋዜጠኛ የነበሩት ያለው አክሊሉ “አሻሮ መንጋ” የተሰኘ የፖለቲካ መፅሐፍ ለንባብ በቃ፡፡
መፅሐፉ በአገራችን ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተወሳሰበ የመጣውን የፖለቲካ ሁኔታ፣ በፖለቲካና በፓርቲ መከታነት የግል ጥቅምን የሚያሳድዱ ግለሰቦች ሁኔታን ይዳስሳል ተብሏል፡፡ በተጨማሪም በግለሰብ ሰብዕና፣ በፅናትና ፍቅር፣ በጥላቻና ቅጥፈት፣ በመቻቻልና ጊዜ በማያደበዝዘው የሀገር ፍቅር ስሜት ላይ አተኩሮ፣ የዘረኝነት በሽታ በወቅቱ እልባት ካልተበጀለት የሚያመጣውን መዘዝም የሚተነትን እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል፡፡
“የኛ ፓርቲ ገና አልተወለደም” የሚሉት ደራሲው፤ ለአገር ይጠቅማሉ ያሉትን ጠቃሚ ነጥቦች ሁሉ በመፅሐፉ ውስጥ ማካተታቸውን ተናግረዋል፡፡
በ300 ገጾች የተቀነበበው መፅሀፉ፤ በ101 ብር ከ60 ሳንቲም ለገበያ ቀርቧል፡፡ ደራሲው ከዚህ ቀደም ለሆሄ የስነፅሁፍ ሽልማት እጩ ለመሆን የበቃውን “ወሰብሳቤ” የተሰኘ መፅሐፍ ለንባብ ማብቃታቸው የሚታወስ ነው፡፡

Read 1537 times