Saturday, 09 December 2017 13:41

የእርሻ ውጤቶች አውደ ርዕይ በሚሊኒየም አዳራሽ እየተካሄደ ነው

Written by  መንግሥቱ አበበ
Rate this item
(0 votes)

 5ኛው አዲስ የእርሻ ምግቦችና የፓኬጂንግ ዓለም አቀፍ አውደ ርዕይ፣ ትናንት ኅዳር 29 በሚሊኒየም አዳራሽ የተከፈተ ሲሆን እስከ ሰኞ ታህሳስ 2 ቀን 2010 ዓ.ም ይቀጥላል ተብሏል፡፡  
በዚህ አውደ ርዕይ ላይ ከቱርክ፣ ከጀርመን፣ ከሕንድ፣ ከፈረንሳይና ከኢትዮጵያ የተውጣጡ 73 ኩባንያዎች በእርሻ፣ በእርሻ መሳሪያዎች፣ በምግብ፣ በምግብ ቴክኖሎጂዎችና የማሸጊያ መሳሪያዎች እንደሚያቀርቡ ታውቋል፡፡
የአውደ ርዕዩ አዘጋጅ የኢቴል ማስታወቂያና ኮሚኒኬሽን ማኔጂንግ ዳይሬክተር ወ/ሮ ሃይማኖት ተስፋዬ፤ አገራችን ወደ ኢንዱስትሪው ኢኮኖሚ እየተሸጋገረች ቢሆንም ይህ አውደ ርዕይ በእርሻ ኢንዱስትሪ አዳዲስ ቴክኖሎጂ በማስተዋወቅ የእርሻውን ዘርፍ የሚያጎለብት ይሆናል ብለዋል፡፡
በአውደ ርዕዩ ላይ የሚሳተፉ የውጭ አገር ኩባንያዎች፣ ከአገር ውስጥ ኩባንያዎች ጋር የንግድ ትስስር እንደሚፈጥሩ፣ ቀደም ሲል በተደረጉ አውደርዕዮች ቦሽና አንካራ የተባሉ ኩንባያዎች የንግድ ትስስር መፍጠራቸውም ታውቋል፡፡

Read 1106 times