Print this page
Saturday, 09 December 2017 13:59

ጅቡቲ ከኢትዮጵያ ንፁህ የመጠጥ ውሃ በነፃ ልታገኝ ነው

Written by  አለማየሁ አንበሴ
Rate this item
(2 votes)


    95 በመቶ የኢትዮጵያ የውጪ ገቢ ንግድ የሚተላለፍባት ጅቡቲ፤ ከ3 ወራት በኋላ ዜጎቿ የኢትዮጵያን ንፁህ የከርሠ ምድር የመጠጥ ውሃ በነፃ ያገኛሉ ተብሏል፡፡ በምስራቅ አፍሪካ ሃገራት የጅቡቲ አምባሣደር ሻሜቦ ፊታሞ አዴቦ ለቱርክ መንግስታዊ መገናኛ ብዙሃን አናዶሉ እንደገለፁት፤ አንድ ሚሊዮን ለማይሞላ የጅቡቲ ዜጎች በቀን 104 ሺህ ኩዩቢክ ሜትር ንፁህ የመጠጥ ውሃ ከኢትዮጵያ ማግኘት ተችሏል- ብለዋል፡፡
ከሰሜን ምስራቅ ኢትዮጵያ ኦዲጋላ ከርሠ ምድር የሚመነጨውን ይህን ንፁህ የመጠጥ ውሃ ለማስተላለፍም የቧንቧ መስመር ዝርጋታዎች መጀመራቸውንና በቀጣይ 3 ወራት ተጠናቀው ውሃ ማቅረብ እንደሚጀመር አምባሣደሩ አስታውቀዋል፡፡
የጅቡቲ በልበላ ከተማ ነዋሪዎች ደግሞ ከወዲሁ ከኢትዮጵያ የሚመነጭ ንፁህ ውሃ ተጠቃሚ መሆን መጀመራቸውንም አምባሳደሩ ጠቁመዋል፡፡ የሁለቱ ሃገራት ህዘቦች በደም የተዋሃዱ ናቸው ያሉት አምባሣደሩ፤ ጅቡቲያውያኑ ከኢትዮጵያ ንፁህ የመጠጥ ውሃ በነፃ ማግኘታቸው የህዝቦችን የእርስ በእርስ ትስስር ያጠናክራል ብለዋል፡፡ ኢትዮጵያ ለጅቡቲ በነጻ ታቀርባለች ለተባለው ንጹህ የመጠጥ ውሃ በለውጡ ምን እንደምታገኝ አምባሳደሩ ያሉት ነገር የለም፡፡  
95 በመቶ የኢትዮጵያ የወጪ ገቢ ንግድ መተላለፊያ የሆነችው ጁቡቲ፤ በየዓመቱ ወደቧን በማከራየት ከኢትዮጵያ በቢሊዮን ዶላሮች የሚቆጠር ገቢ ታገኛለች፡፡

Read 2190 times