Saturday, 09 December 2017 14:00

ዳሸን ባንክ ለተለያዩ ተቋማት 4.1 ሚሊዮን ብር ለገሠ

Written by  መንግሥቱ አበበ
Rate this item
(4 votes)

 ዳሸን ባንክ ሕዳር 21 ቀን 2010 በሸራተን ሆቴል ባደረገው የባለ አክሲዮኖች ጠቅላላ ጉባኤ ማኅበራዊ ኃላፊነትን ከመወጣት አኳያ ለሀገርና ለወገን ጠቃሚ ናቸው ያላቸውን በጎ ተግባራት ለመደገፍ 4.1 ሚሊዮን ብር ለገሠ፡፡
በዚህ መሠረት በጣና ሐይቅ ህልውና ላይ አደጋ የደቀነውን የእንቦጭ አረም ለማስወገድ የሚደረገውን ጥረት ለማገዝ፣ ለአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ሁለት ሚሊዮን ብር፣ የለገሰ ሲሆን ለኢትዮጵያ የልብ ሕሙማን ህፃናት ማኅበር መርጃ፣ ለኢትዮጵያ ካንሰር ማኅበርና ለሙዳይ በጎ አድራጎት ማኅበር ለእያንዳንዳቸው 700 ሺህ ብር ድጋፍ አድርጓል፡፡ ባንኩ በዕለቱ ባደረገው ጠቅላላ ጉባኤ፣ የባንኩን የተከፈለ ካፒታል በ700 ሚሊዮን ብር ለማሳደግ የወሰነ ሲሆን የሥራ ዘመናቸውን ባጠናቀቁ የዲሬክተሮች ቦርድ አባላት ምትክ ዘጠኝ አዲስ አባላት መርጧል፡፡

Read 2363 times