Sunday, 24 December 2017 00:00

በሀሳብ መንገድ ላይ

Written by  ተመስገን
Rate this item
(2 votes)

 “ሞኝነቱን ያወቀ ሞኝ አይባልም!”
              
   ታላቁ ቮልቴር የሰር አይሳክ ኒውተን ወዳጅ ነበር። ኒውተን በሞተበት ጊዜም በቀብር ስነ ስርዓቱ ላይ ተገኝቷል፡፡ ቮልቴር “.. ለእንግሊዞች የተፃፈ ደብዳቤ” .. በሚለው ማስታወሻው ስለ ኒውተን ታላቅነት ሲያወሳ፡-
“በታሪክ ውስጥ ታላቁ ሰው ማነው? … ቄሳር … አሌክሳንደር .. ታመርሊን ወይስ ክሮሞዌል?” … ተብሎ ሲጠየቅ፡-
“ታላቅ መሪ ማለት ሌሎችን በጉልበቱ ወደ ባርነት የማይቀይር፣ ዕውነትን የሚቀበልና እኛነታችንን የሚረዳ” (… for it is to him who masters our minds by the force of truth and not to those who enslaves them by violence, that we owe our reverence” … በማለት እንደመለሰ ይነግረናል፡፡
“እኔ ፖለቲከኛ አይደለሁም” … ይላል ቮልቴር። … ስለ ራሱ ደግሞ ሲናገር፡፡ ነገር ግን ሌሎች ሰዎች በራሳቸው ክብር ያላቸው ስለመሆኑና ማንም ሊያሞኛቸው እንደማይገባ እከራከራለሁ፡፡ (… Politics is not in my line; I have always confind myself … to doing my little best to make men less foolish) .. ብሏል፡፡
ወዳጄ፡- ሁለቱ ሊቃውንት እንዳሉት ሌሎችን ማሞኘት፤ ነፃነታቸውን ማሳጣት፣ ግዛታቸውን መቀማት፣ ዳቦአቸውን መንጠቅ፣ ከሁሉም በላይ ደግሞ የማይፈልጉትን ማንነት መጫን አሳፋሪ ነው። ሰዎች ተጋግዘው፣ ተቻችለው፣ ተዋደውና ተጋብተው መኖራቸው፣ ለጋራ ልማትና ጥቅም ባንድነት መቆማቸው፣ የአገራቸውንና የአካባቢያቸውን ሰላም ማስከበራቸው … አስፈላጊነቱንና የአብሮነታቸው ጌጥ መሆኑን ስለተገነዘቡ እንጅ በሰላም ስም ጭቆናን ለመቀበል፣ በሰላም ስም የማይፈልጉት ማንነት እንዲጫንባቸው አይደለም፡፡
“የተፈጠርኩት ለሰላም ነው፡፡ … ሰላምን ምን ያህል እንደምወድ እግዜር ብቻ ነው የሚያውቀው፡፡ … ነገር ግን በሰላም ስም ጭቆናን የምቀበል ፈሪ አይደለሁም!!” (… I am a man of peace. God knows how I love peace; … but I hope, I shall never be such a coward as to mistake opression for peace”) … በማለት ይህንኑ ሃቅ ያረጋገጠልን ደግሞ ኮሱቱ (Kossuto) ነው፡፡
ወዳጄ፡- ብዙዎች ባንዱ፣ አንዱ በብዙዎች ውስጥ መኖሩ የተረጋገጠ ጉዳይ መሆኑ እንዳለ ሆኖ … እያንዳንዱ ሰው …  የየራሱ ግላዊ ሃሳብ፣ የየራሱ እምነት፣ የየራሱ ምኞትና የህይወት ትርጓሜ … ባጭሩ የየራሱ “እኔነት ወይም ማንነት” … እንዳለው መዘንጋት የለበትም። እያንዳንዱ ሰው የየራሱ ታሪክ አለው፡፡ … ታሪኩ አብሮት ከሚኖረው፣.. ወይ ከፈለቀበት አካባቢና ህዝብ ጋር በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ሊዛመድ ወይ ሊጠላለፍ ይችላል፡፡
ዓለምን ያንቀጠቀጡ አብዮቶች፣ የብዙ ሚሊዮን ህዝቦችን ልብ የገዙ እምነቶች፣ በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ሰዎችን ያስፈጁ ጦርነቶች፣ ስልጣኔያችንን ከፍ ያደረጉ ፈጠራዎችና ግኝቶች ተያያዥነት ያላቸው ስር ምክንያቶች ቢኖራቸውም ለውጤት የበቁት በግለሰቦች የግል ችሎታና ብቃት መሆኑ ይነገራል፡፡
አጋጣሚ በሚፈጥራቸው ሁኔታዎች አንዳንድ ሰዎች ሃሳባቸውን፣ ዕውቀታቸውን፣ ስሜታቸውን፣ ጊዜያቸውንና ገንዘባቸውን በመጠቀም በምድራችን ገጽ ላይ በበጎም ሆነ በክፉ ቀለማት … “እኔነታቸውን” … መሳል ችለዋል፡፡ … ይህም ታሪካቸው የግልም፣ የማህበረሰብም እየሆነ ይጠቀሳል፡፡
(Men could make their own history … but not under circumstances chosen by themselves,… but under the circumstances, encountered, given and transmitted from the past) … በማለት ካርል ማርክስ አብራርቶታል፡፡
ወዳጄ፤ “ሰው ማለት ሃሳብ ነው፡፡” … A man is what he thinks… ይባላል፡፡…ሃሳብ ከሌለህ ምንም ነህ።… ሃሳብ ካለህ ደግሞ ሰው!!... እንደ ማለት ይመስላል፡፡… ሃሳብ የሌለው ሰው ደግሞ የለም፡፡ ስለዚህ ሰው “ምንም” ነው መባሉ ፉርሽ ይሆናል፡፡…እዚህ ላይ ‹ሃሳብህ› ማንነትህ ሆነ ማለት፣ ‹ማንነትህ› ደግሞ ሃሳብህ ነው ማለት ነው፡፡…. የሚጨመር፣ የሚቀነስ ነገር የለውም፡፡… ሰው ተረት አይደለም!!
የኛን ጉዳይ እንደ ምሳሌ ብናነሳ…መጀመሪያ እንደ ሰው የማሰብ ነገር እንደተጠበቀ ሆኖ…አንድ ሰው ‹ኢትዮጵያዊ ነኝ›…. ካለ…እንደ ኢትዮጵያዊ አስባለሁ ማለቱ ነው፡፡… ሃሳቡ ማንነቱ ስለሆነ!!... ከሶስት ከአራት አያቶች የተገኘ ፍሬ ሊሆን ይችላል፡፡… መታወቂያ ለመውሰድ አንዱን ምረጥ ብሎ ነገር ምንድ ነው?... የተቆራረሰ ማንነት አለ እንዴ?... ማንነት እኮ ሀሳብ ነው!!!
“Learn to trust your own nature, your own identity. Accept it, like it, reveal it, don’t suppress it;… don’t attempt to shade it with little lies and half truths. When you do you miss so much of life and happiness that can be yours” ራስህን እመን፣ ተፈጥሮህን ውደደው፣ አትዋሸው፣ አትጨቁነው…በይፋ ተናገር፡፡… አለበለዚያ የራስህ የሆኑትን የህይወት በረከቶች ትገፈፋለህ፣ ደስተኛ አትሆንም”… የሚለን ሃሪ ብራውን ነው፡፡… ለንደ’ኔ ዓይነቶቹ ኢትዮጵያውያን፤ “መታወቂያችሁን ወስዳችሁ እኛነታችንን መልሱልን” በሉ አያሰኝም?
ወዳጄ፤ ወደ ተነሳንበት ስንመለስ፣ አይሳክ ኒውተን “በታሪክ ውስጥ ታላቁ ሰው የሌሎች መብት የሚያከብር ነው”… ብሎ ነበር፡፡… “በተቻለኝ መጠን ሰዎች እንዳይሞኙ እለፋለሁ”… ያለን ደግሞ ታላቁ ቮልቴር ነው፡፡ “ሞኝነቱን ያወቀ ሞኝ አይባልም” (He, who knows that he is a fool…is no more a fool) ያለንስ ማነው?
ሠላም!!!

Read 698 times